Friday 14 November 2014

በድል ነሺው ስምህ …


                             Please read in PDF

በጐነት ለዛ አጣ፤
ወዳጅ ከወዳጅም ፥ ፍቅሩ ሆነ ለበጣ፤
መልክ ብቻ ሆኖ፤
እምነት ከኃይል ጦሞ …
ኪሳራ ገነነ፤

በደሉ ጨመረ፤
ርኩሰቱ ነፈረ፤
.
.
.
ነውሩ ሰማይ ነካ፤
ግፍ እንደʻህል ቦካ፤
መኖርም መሞትም አንድ ሆነብን ውሉ፤
እባክህ ጌታ ሆይ፦
የዓይኖቻችን ብሌን ፣ ያንተን ማዳን ይዩ፤
ትውልድ ያቀለጠው ፣ የኃጢአትም ዋዕዩ፤
በድል ነሺው ስምህ ፣ ይቀጥቀጥ ይሸነፍ፤
ከዚህ የተነሳ፦

ይሁን ለትውልዱ ፣ ከስቃዩ ማረፍ፡፡

1 comment:

  1. አሜን የሕይወትን ቃል ያሰማህ፤ ጸጋህ ይብዛ።

    ReplyDelete