Tuesday 2 September 2014

ማስተስረያውን ክዶ


                               Please Read in PDF 


ሳይጐድል ደምግባቱ፣ አምሮ እንደደመቀ፤
ትኩስ ሥጋነቱ፣ ግሎ እንደሞቀ፤
ሸጋ ቆንጆነቱ፣ ጉድ አጀብ አስብሎ፤
ከደሙ ቤዛነት፣ ከ‘ርሱ ተነጥሎ፤

በዝና አድናቆት፣ ከፍ ከፍ ብሎ …
ለመዳን መመኘት፣
ህልም ነው መቃዠት …

የማለዳ ውድቀት፣ እየሳቁ መርዶ፤
የአዲሱን ኪዳን ደም፣ በንቀት አክፋፍቶ፤
ወደአብ ለመቅረብ ማስተስረያውን ክዶ፡፡


No comments:

Post a Comment