Monday 24 June 2013

ኪዳን አለኝ እኔ

Please read in PDF - kidan alegn ene

ንፋሱን ቀስቅሰው
ሞገዱን አናውጠው
ቀስትህን ገትረው
ሰይፍህን ሰይፈው

አሹለው ጥርስህን
ከስክሰው ፊትህን
ግንባርህን ቋጥረው
ቁጣህን ተቆጣው
ጩኸትህን ጩኸው
ጭፍራህን ቀስቅሰው
ወድረው ጦርህን
ዘርጋው ወጥመድህን
ጉድጓዱንም አስፋው
ጅራፍህን ግመደው …
የቤቴን ምሰሶ አብዝተህ ነቅንቀው
ከፊቴ ያለውን ሁሉንም ውሰደው …
እንዲህ ተግዳሮትህ ገንፍሎ ሲወጣ
ብዙ ይጠቅመኛል በነፍሴ ልሠራ፡፡
ይደንቀኛል ክንዱ የጌታ ፈቃዱ
ሰልፉን ለእጆቼ ሲያሳይ በጥበቡ
ካ’ንተ ሺህ ተግዳሮት ብዙ ዘመን ቀድሞ
ኪዳን አለኝ እኔ፥
ንፋስህ ላይነቅለው ጎርፍህም ላይነካው የእኔን ቤት ፈጽሞ፡፡



1 comment: