Sunday 2 June 2013

ንስሐውም ይሁን…


ለአደባባይ ኃጢአት
ሌላም ለበደለ በሚገድል ስህተት
ትውልድ ለሚሻገር ለማያቆም ግድፈት
እልፍ ላሰናከለ

በጥቂት ፅድቅ ለታጀለ
የነፍሶች ሕሊናን ወግቶ ላቆሰለ
በክፋት ፍላፃ አልሞ በገሀድ
ሁሉን አሳድሞ ወደራሱ መንገድ
አስጨፍሮ አስኮብልሎ
በጉቦ ቃል ፍትሕ ረግጦ
ጦር አንግሦ ሰላም ጠልቶ
እንዲህ ኖሮ ኖሮ ተመልሻለሁ ሲል
ባይቸኩል ምናለ ከንቱ ለማገልገል
ምነው እንደ ኃጢአት ምነው እንደነውሩ
ንስሐው ይቅርታው ቢተርፍ ለሀገሩ
ኃጢአቱ በገሐድ ከተሰራ ባዋጅ
ትውልድ እንድንፈውስ ዘመኑን እንድንዋጅ
ንስሐውም ይሁን በየአደባባዩ
በቀል ቂሙ ጠፍቶ
ይቅርታው ጎምርቶ
አንድ ሆነን ስንዘምር መቅደሱ ተሞልቶ
ያላመነው እንዲያምን
 ያመነው እንዲጸና በሕይወት ተሰብኮ፡፡


1 comment: