Monday 17 June 2013

የተረሳን ለሚያስቡ

Please read in PDF

አውቃለሁ ዘመኔን፥ ከንቱ ያለፈውን፤
በስርቆት በዝሙት፥ በስካር በዘፈን፤
በአድመኝነት ቁጣ፥ በክርክር ቅናት፤
በሽንገላ ፍቅር፥ በርኩሰት መዳራት …

ምራጭ እንደሆንኩኝ፥ የሰው መጨረሻ፤
መንፈሴ ያደፈ፥ ሥጋዬም ቆሻሻ፤
አውቃለሁ መሆኔን፥ ፍጹም በደለኛ፤
ነፍሰ ገዳይ አሳች፥ ቀጣፊ ቀማኛ፤
ብዙ ያሰናከልኩ፥ የዕንቅፋት ድንጋይ፤
የማልረባ ብኩን፥ ዋሾ የቃል አባይ፤
አውቃለሁኝማ …
ፍጻሜዬ ከንቱ፥ ከንቱ ከንቱ ከንቱ፤
ያለጌታ ምህረት፥ ያለቸርነቱ፡፡
በአንዱ ክንፌ ጌታ፥ ኃጢአቴን ልናዘዝ፤
በአንዱ ክንፌ ደግሞ፥ በፀጋህ ልታገዝ፤
በ’ኒህ ሁለት አክናፍ፥ በርሬ በርሬ፥ ወደአንተ ስመጣ፤
ጥርስ ፉጨትና ለቅሶ፥ አይሆን የ’ኔ ዕጣ፤
ግና የ’ኔ ጌታ…
‹‹ ሌባ እናት ልጇን፥ አታምንም›› እያሉ፤
የቀደመ ነውሬን፥ ዛሬም ያወራሉ፤
አንተ ረስተኸዋል፥ እነርሱ ያውቃሉ፡፡
እባክህ እርዳቸው፤
ከንቱ አትተዋቸው …
የጠቢብ አይኖቹ፥ በራሱ እንዲሉ፤
አይናቸውን ከሰው፥ ነቅለህ ጣልላቸው፤
አፋቸው ስለሰው፥ ማውራቱን ይዘንጋው፤
የእድሜያቸውን ሙሉ፥ አመፃ አበሳ ያውሩት ለራሳቸው፥
                         ላ’ንተም ቅዱስ ጌታ፤

እኔም አረፍ ልበል፥ ለእነርሱም ይቅርታ፡፡

No comments:

Post a Comment