Wednesday 19 June 2013

ቀድማችሁ ተሰሩ

አብርሃም ተስፋውን በብዙ ሊቀበል
ብዙ አሥርት ዓመታት ፍፁሙን ታግሷል
ሕዝቡን እንዲመራ ቅዱሱ ሲጠራ

ሰማንያ ዓመታትን ሙሴ ጻድቅ ነብይ በእጁ ተሠራ፡፡
የልዑልን መንገድ ጠራጊውን ሊወልድ
ዘካርያስ ካህን ፀንቷል በአገልግሎት
አብንና እኛን ሊያገለግል ጌታ 
ሠላሳ ዘመናት ኖሯል በዝምታ፡፡
የመሠራት ዘመን ከአገልግሎት በልጦ
የአገልግሎት ዘመን ከመሠራት አንሶ
በፍጹም ማስተዋል ሩጫቸውን ሮጠው
ለእግዚአብሔር መንግሥት መንጋ ምርኮ አብዝተው፡፡
የሕይወት መምህራን እንዲህ ካስተማሩ
ምንድን ነው ችኮላው ታይቶ መሰወሩ?
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
ሳይሠሩም መሮጥ አረም ያስታቅፋል፡፡
እናንተ አገልጋዮች ቀድማችሁ ተሠሩ
ሮኆቦት እንዲሆን እንዲሰፋ መከሩ፡፡


No comments:

Post a Comment