Friday 8 July 2022

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፯)

 Please read in PDF

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን የምሥራቃውያን ትምህርት

የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን፣ ከትውፊት ነጥለው ብቻውን በማቆም ሥልጣኑን ይቀበላሉ። ከትውፊት የመነጠላቸውም ምክንያት፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትውፊት የበላይና የቤተ ክርስቲያን መመሪያ፣ የኹሉ ነገር መመዘኛ፣ ልዩና የማይገረሰስ ሥልጣንም እንዳለው አምነው ይቀበላሉ።



ከካቶሊክና ከላቲን አብያተ ክርስቲያናት በተለየ መንገድ፣  የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መጽሐፍ ቅዱስን ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መነጠላቸውና “ብቻውን በቂና አስተማማኝ” ማለታቸው የሚደንቅ ነው።

ይህን ለማለት የሚያበቁ ምክንያቶችንም ሲዘረዝሩ፦

1.   የሐዋርያት ሥልጣን አብቅቶአል፦ ይህ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን የመጻፍ ሥልጣን ተዘግቶአል፤ ስለ ተዘጋም ማንም ሰው ስድሳ ሰባተኛውን መጽሐፍ ቅዱስ መጻፍ ወይም ከቅዱሳት መጻሕፍት ተቃራኒ ዐሳብ ያለውን ትምህርት ማምጣት አይችልም። ምንም እንኳ የሐዋርያነት አገልግሎቱ ዛሬም ድረስ መኖሩን ባያስተባብሉም፣ ሥልጣኑ ግን ማብቃቱን ብዙዎቹ ያምናሉ፤[አንዳንዶች ግን የሐዋርያነቱ ሥልጣኑ ብቻ ሳይኾን አገልግሎቱም ጭምር ማብቃቱን ያምናሉ]፣

2.   ቅዱሳት መጻሕፍትን የጻፈው ሰው ልዩ መገለጥ አለው፦ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው፣ መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶአል ወይም ተነቃቅቶ ጽፎታል፤ (1ጴጥ. 1፥21)። በመነዳቱና በልዩ መገለጡም ውስጥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚል መልእክት አለ ተብሎም ፍጹም ይታመናል።

ከዚህም የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ኹሉም፣ ከእግዚአብሔር የኾነ እውነተኛ ልዩ መገለጥና ትክክለኛ የሕይወት ቅድስና ነበራቸው።

3.   ሥልጣናዊ ኾነው የጻፉአቸው መጻሕፍት፣ ከሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትና የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ተስማሚና ስሙር ናቸው፤ ስለዚህም አንደኛው ኪዳን የሌላኛው ኪዳን ትርጕምና አካል ነው።

4.   የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተጻፉበት ወራት ሐዋርያዊ ሥልጣን አላበቃም። የተጻፈውም ሐዋርያዊ ሥልጣን ባላበቃበትና ባልተጠናቀቀበት ወራት የተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው። ለብዙዎች ጥያቄ የሚኾነው፣ ሐዋርያዊ ሥልጣን (Apostlic authority or sessesion) ምንጩ ምንድር ነው? ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ፤ ለዚህም መልሱን የምናገኘው ከዚያው ከቅዱሳት መጻሕፍት ነው፤ (ለምሳሌ፦ ሐዋ. 1፥21-22 ማንሳት እንችላለን)።

5.   ቅዱሳን ሐዋርያት ተልዕኮና ሥልጣንን የተቀበሉት በቀጥታ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በተለይም ደግሞ ለሐዋርያነት የመረጣቸውና “ሐዋርያት” ብሎም የሰየማቸውም ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብል ያምናሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለሐዋርያነት ብቁ ተደርገው ከቀረቡት መስፈርቶች አንዱ የጌታችንን ትንሣኤ ወይም ኢየሱስን ከሙታን ትንሣኤ በኋላ ፊት ለፊት መመልከት የሚለው ሌላኛው ትልቅ እማኝ ነው።

6.   በሐዋርያዊ ሥልጣን የጻፉአቸው ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የሰዎችን ሕይወት የሚለውጡና ለውጠውም ለምስክርነት የበቁ ናቸው፣

7.   በመንፈስ ቅዱስ መነዳት የተጻፉት ቅዱሳት መጻሕፍት ለቤተ ክርስቲያን አምልኮ በቀጥታ ለግልጋሎት የሚውሉና የሚጠቀሙባቸውም ነበሩ።

ስለዚህም “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” የሚለው ቃል በቀጥታ የሚገናኘው ከካቶሊካዊት[1] ቤተ ክርስቲያን ምልከታ ነው። “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት” ተብሎ የሚታወቀው ደግሞ  በኦርቶዶክስ ወይም በምሥራቃውያን ዘንድ ነው።

እኒህና ሌሎች አያሌ ምክንያቶችን በመጥቀስ፣ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ትምህርቶቻቸውን የሚጠሩት “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች” በማለት ሳይኾን፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” በማለት ነው። ለዚህም ጥቂት ዋቢ እንጥቀስ፦

“ … እነዚህም መጻሕፍት ከሌሎቹ ኹሉ ተለይተው “መጻሕፍተ አምላካውያት” ይባላሉ፤ ምክንያቱም የአምላክን ነገር የሚናገሩ የአምላክ ቃል የተጻፈባቸው ስለ ኾኑ ነው። እነርሱም የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው። አሥራው መጻሕፍትም ይባላሉ፤ ይህም ማለት ብሉይና ሐዲስ ለቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ኹሉ ሥር መሠረት ስለ ኾኑ …”[2]

“እነዚህ የተጠማ በውስጣቸው በሚገኙ ቃላት ይረካ ዘንድ የእውነተኛ ድኅነት (መዳን) ምንጮች ናቸው፤ በእነዚህ ብቻ የቅድስና ትምህርት ይሰበካል። ከእነዚህም ማንም ምንም መጨመር ወይም መቀነስ አይችልም።” ብሏል። ስለ ተነባቢዎቹ (ንባባውያት) መጻሕፍት ደግሞ፡- “... ከሚቀነኑት መጻሕፍት ጋር ያልኾኑ ነገር ግን ዐዲስ ለሚመጡትና ትምህርተ ክርስትናን ለመማር ለሚፈልጉ ይነበቡ ዘንድ በአባቶች የታዘዙ ሌሎች መጻሕፍት እንዳሉ አስፈላጊ መኾኑን እጨምራለሁ”[3]

ይቀጥላል …


[1] “ካቶሊክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያን መገለጫ የኾነ ስም የሮም ቤተ ክርስቲያን የግል መጠሪያዋ ብታደርገውም፣ መጀመሪያ ላይ ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለው ቤተ ክርስቲያን በኹሉ ዘንድ ያለች መኾኗን ለማመልከት ነው። የኪዳነ ወለድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት “ኮቶሊክ” (በጽርዕ ካቶሊክ) የሚለውን ቃል የሚፈታው “የቤተ ክሲያን ስም፣ ኵላዊ ዘኵሉ እንተ ላዕለ ኵሉ” በማለት ነው (ገጽ 552)።

ቅዱስ አትናቴዎስም ቃሉን የተጠቀመው ይህን የቤተ ክርስቲያን ማንነት መሠረት በማድረግ ነው። እርሱ በኹሉ ዘንድ ያለች ቤተ ክርስቲያንን በሚወክል አገላለጽ ያቀረበውን መልእክት ታዲያ፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሓፊ የአትናቴዎስን ሐሳብ በመለወጥና የእርሱን ስመ ሃይማኖት ወደሚገልጠው መጠሪያ ለውጦ በመተርጐም መልእክቱን አዛብቶታል።    

[2] አበራ በቀለ (ሊቀ ጉባኤ)፤ ገጽ 54

[3] ዶ/ር ዲበኵሉ ዘውዴ፤ 81 ቅዱሳት መጻሕፍትና ምንጮቻቸው ቀኖናት፤ 1987 ዓ.ም፤  ገጽ 48-54።

6 comments:

  1. All what you said is true. except You mentiond in your last sentence 'THE GLORY OF TRINITY COVER THE EARTH" Is there any place that say Trinity in the Bible? Where did you get it?

    ReplyDelete
  2. pls Can you show me one verse in the Bible That says God is Trinity? Ab Wolde M/Kidus is One God not Three ( Trinity).

    ReplyDelete
  3. ABE, WOLDE,MENFES KIDUSE .THIS IS TRINITY AND YOU CAN FIND IT ALLOVER IN THE BIBLE IF YOU WANT.

    ReplyDelete
    Replies
    1. I am not writing to argue but to know the truth. The word Trinity is not in the Bible. God strictly said that He is the only one and there is no one beside Him. God is a Spirit and manifested in flesh but that doesn't mean He is Trinity. The father the Son and the Holy Spirit is one God not Trinity.

      Delete
  4. you are not christian, if you don't know the holy Trinity, you are either Mormon or only Jesus. please find any christian and ask this question or contact this website owner.

    ReplyDelete
  5. አብ + ወልድ + መንፈስቅዱስ = እግዚአብሔር = ሥላሴ

    ሥላሴ ወይም Trinity የሚለው፣ ቃል በቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ባይገኝም በትርጉም ግን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ለማመልከት የምንጠቀምበት ቃል ነው።
    የይሖዋ ምስክሮች ይህንን አገላለጽ ስለማይቀበሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ አለመገኘቱን አንድ መከራከሪያቸው ያደርጉታል። በብዙ የክርስትና ተከታይ ግን ከላይ በሂሳብ መልክ የቀረበውን ይቀበላሉ።

    ReplyDelete