Tuesday 3 November 2020

ባልፈጠረው ፍጥረት ...

 Please read in PDf

ከተገባደደ ከተጠናቀቀ

ኹሉም ከተሠራ ካበቃ ካለቀ

በቀን መጨረሻ በፍጥረት ፍጻሜ

ሰው የሚባል ፍጡር ተፈጠረ ያኔ!

ፍጥረቱን ሲያስውብ በምክሩ ሲያደረጅ

ሲያሰማምር ያኔ በፈቃዱ ሲያበጅ

ከያህዌ በቀር አልነበረም ሌላ

ብቻውን አሰበ ብቻውንም ሠራ፡፡

ዳሩ

ሰው ግን ተዐበየ ተበተ በከንቱ

ሰው ብቻ እያለ ልክ እንደ ፈጣሪ ተነፍቶ ማበጡ

ባልፈጠረው ፍጥረት ፈጣሪ ነኝ ብሎ ተነፍቶ ማበጡ!

No comments:

Post a Comment