Thursday 10 September 2020

... ደረስክ የሚባለው...

Please read in PDF

በአሮጌ ሰውነት ቀኑ ቢግተለተል

ዓመት፤ ዓመት ወልዶ ዘመኑ ቢቆለል

ከኹለተኛው አዳም ላልተወለደ አዳም

የአዲስ ዘመን ብሥራት ዓመቱም አልጠባም!

የጨለማው ጭጋግ የተፈለቀቀው

አዲስ የሕይወት ብርሃን የፈነጣጠቀው

በኢየሱስ ላመነ ለአዲሱ ሰው ነው

ዘወትር ለአዲስ ዓመት ደረስክ የሚባለው።

1 comment: