Saturday 16 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፬)


በእስጢፋኖሳውያን ላይ የደረሰው መከራ
   “እብለክሙ ኦ ሕዝበ ክርስቲያን ምዕመናኒሃ ለማርያም ድንግል በክልኤ” ኵሉ ብዕሲ ዘተወክፈ ኪያሆሙ፥ ወዘተሳተፈ ምስሌሆሙ ወዘአንበሮሙ ውስተ ቤቱ ወኀበ ቤተክርስቲያን በውስተ ምድረ ርስቱ እሙኒ ሥዩም ይሠዐር ወይትበርበር ቤተ ንዋዩ፥ ወምድረ ርስቱ ይኩን ለባዕድ።
  ሊቃነ ካህናትኒ ወንቡራነ እድ ወኵሎሙ ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን ወመነኮሳትሂ ወኵሎሙ ሕዝብ ለእመ ተረክቡ እንዘ እኀብኡ ኪያሆሙ፥ ፈድፋደ ኩነኔ ላዕሌሆሙ። ሢመቶሙ ወምድረ ርስቶሙ ይኩን ለካልዕ እስመ ኮኑ ሱቱፋነ ምስሌሆሙ።
  ወእሙንቱሰ ደቂቀ እስጢፋ በአማን አይሁድ እሙንቱ እለ አብዩ ሰጊደ ለማርያም ድንግል በክልኤ ወለ መስቀለ ዋሕድ ወልድ ለእሙንቱሰ ኵነኔሆሙ ሞት።
   ወዘረከቦሙሂ ይኵንኖሙ በፅኑዕ ኩነኔ ወቀቲልሰ ኢይቅትሎሙ፤ አላ ይብጽሖሙ ውስተ ኩርጓኔነ ከመ ንሰማዕ ቃሎሙ። ወከመ ይኩን ፍትሕ ላዕሌሆሙ ወዘተረክበ። ብዕሴ እንዘ ይብሎ ሰላም ለእስጢፋዊ መክፈልቲ ምስለ እለ ተወክፋዎሙ ለደቀቂ እስጢፋ።”
የዚህ አማርኛ ትርጉም፦
“በኹለቱም ጊዜያት ድንግል የምትሆን የማርያም ምዕመናን የኾናችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ እንዲህ እላችኋለሁ። “ማናቸውም ሰው ሁሉ ደቂቀ እስጢፋን የተቀበለ ከእነርሱ ጋር የተባበረ በቤቱ ውስጥም ያኖራቸው ወይም በቤተ ክርስቲያኑና በርስቱም ምድር ያኖራቸው ቢገኝ፥ ሹመት ያለው ከኾነ ከሹመቱ ይሻር፥ ቤቱም ይዘረፍ ገንዘቡ ኹሉና ያለውም የምድሩ ርስት ለባዕድ ይሁን።
ሊቃነ ካህናት፥ ንቡረ ዕድ የቤተ ክርስቲያን ሹማምንትና መነኮሳትም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ እነርሱን ሲደብቋቸው ከተገኙ በእነርሱ ላይ ከፍ ያለ ቅጣት ይፈጸምባቸዋል። ሹመታቸውና የምድር ርስታቸው ለሌላ ይኹን። ከእነርሱ ጋር ተባብረዋልና ነው።
እነዚህ ደቂቀ እስጢፋ ግን ለድንግል ማርያምና ለአንድ ልጅዋ መስቀል መስገድን እምቢ ያሉ ናቸው፥ በእውነት አይሁድ ናቸው። የእነርሱ ቅጣት ሞት መሆን አለበት። ያገኛቸው ሁሉ በጽኑ መከራ ይቅጣቸው። ቃላቸውን ሰምተን በአደባባያችን ሸንጐ እንድንፈርድባቸው ወደ አደባባያችን ያምጣቸው እንጂ መግደልን ግን እርሱ ራሱ አይግደላቸው። እንደዚሁም ከደቂቀ እስጢፋ የሆነውን ሰው አግኝቶ ሰላምታ የሰጠው ሰው ሁሉ ዕድል ፈንታው ደቂቀ እስጢፋን ከተቀበሉ እንደሚደረግባቸው ይኾናል።”[1]  
   የእስጢፋኖሳውያንን መከራ መናገር በራሱ ያምማል፤ አሰቃቂነቱም ኹለንተናው በዲያብሎስ በተወረሰ ሰው የሚፈጸም እንጂ ሰብአዊ የኾነ ሰው እንኳ እንዲህ ሊያደርግ ፈጽሞ አይችልም። ሰው ለሰው ለመራራት ሰውነትን ማየቱ ብቻውን ይበቃዋል፤ ሰው በእንሰሳ ላይ እንኳ የማይፈጸም አሰቃቂ ተግባርን ከፈጸመ ግን ከሰውነት አንሷል ብሎ ደፍሮ መናገር ይቻላል። ታላቁ መጽሐፍ፣ “ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው” (ምሳ. 12፥10) እንዲል፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ልብ ያለው ሰው እንኳ በእግዚአብሔር መልክ ለተፈጠረው ሰው ለእንሰሳ እንኳ ይራራል። እናም ለእንሰሳ መራራት የሚቻለው ሰው፣ ለሰው መራራት ከተሳነው መንፈሳዊነቱ ደባይቷል ማለት ነው።

  እንግዲህ አፄ ዘርዓ ያዕቆብና ሌሎችም ነገሥታት ቢኾኑ እንኳን ለእንሰሳ ለሰዎች መራራት ተስኗቸው ያደረሱት መከራ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፤ በተለይም ዘርዓ ያዕቆብ ፈጽሞ እንኳን መንፈሳዊነት ሰብአዊነት እንኳ ሊታይበት በማይችልበት መልኩ በእስጢፋኖሳውያን ላይ ያደረሰው መከራ እጅግ አሰቃቂና እጅግ ሰቅጣጭ ነው፤ በጥቂቱም በእስጢፋኖሳውያን ላይ የደረሰውን መከራ ከተአምረ ማርያም፣ በአንደኛና ኹለተኛ ገድለ አኀው፣ በአባ እስጢፋኖስ ገድል፣ “ደቂቀ እስጢፋኖስ” በሕግ አምላክ [በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ]፣ ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጐ [በመሪጌታ ኤልያስ ግርማ] እና  እንዲሁም ከሌሎች ገድላቸውና በእነርሱ ዙርያ ከተጻፉ መጻሕፍት በማውጣጣት ከዚህ በታች እንዲህ ማስቀመጥ ይቻላል።
    ንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብ በቅዱሳኑ ላይ እንዲህ ያለ አሰቃቂና መራራ መከራና ስቅየትን አድርሶባቸዋል፦
1.     ላሳቸውን አስቆርጧል፤[2]
2.    ፍንጫቸውን አስፎንኗል፤[3]
3.    ድንጋይ አስወግሯቸዋል፤[4]

4.    በቤት ዓምድ በማንጠልጠል ጪስ አሳጥኗቸዋል፤[5]
5.    ሰውነታቸውን እበት በመለቅለቅ የምድጃ ዓመድ አስደፍቶባቸዋል፤[6]
6.    በግንድ ሽንቁር ውስጥ ጠጠር አስጨምሮ ከሥጋቸው ጋር በአንድነት እንዲቀረቀር አስደርጓል፤[7]
7.    የዘርዓ ያዕቆብ መለኮሳት የእስጢፋኖሳውያንን እግር በዱላ ሰብረዋል፤ ሴት መነኮሳዪቶችንም በማነቆ አድርገው እጅና እግራቸውን መነኮሳቱ አስረዋቸዋል፤[8]
8.    የንጉሡ መነኮሳት አባ ብእሴ ሰላምና አባ ሳሙኤል የተባሉት፣ እስጢፋኖሳውያንን፦ “እነዚህ ቅዱሳን ጸረ ማርያም ናቸው። ለንጉሥ አይታዘዙም፥ ለክብሩም አይሰግዱም ...” በማለት ከሷቸዋል፤ ንጉሡም ባለመስገዳቸው ምክንያት እንዲገደሉ አዝዟል፤[9] እኒሁ መነኮሳት ሃያ የሚያህል መነኮሳትና መነኮሳዪያትን አስገድለዋል፤[10] ልብሳቸውን፣ አስኬማቸውን ቀበቶአቸውን ኹሉ ከዘረፉ በኋላም ራቁታቸውን እሳት አንድደውባቸው በዙርያቸው በከበሮና በክራር እያዜሙ እንዲቃጠሉ አድርገዋል፤


9.    ሰድቧቸዋል፣ አሽሟጦባቸዋል፣ አፊዞባቸዋል፤[11]
10.  ራቁታቸውን በሕዝብ አደባባይ በማቆም እንደ እንሰሳ አስቁሞ አዋርዷቸዋል፤[12]
11.    በቀጋ እሾኽ፣ ጤጤ [ጤጠይ] በሚባል መግረፊያ ጅራፍ፣ በዘንግ፣ በዱላ፣ በበትር፣ በሺመል ከግንድ ጋር ወይም እጅና እግራቸውን በአንድነት አሳስሮ፣ አጋድሞ ደማቸው እስኪፈስ፣ አእምሮአቸውን እስኪስቱ ድረስ አስገርፏቸዋል፤ አስደብድቧቸዋል[13]
  “ … አባ እስጢፋኖስ ኹለንተናው በደም እስኪወረስ ድረስ ወታደሮቹ እየተፈራረቁባቸው በንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብ ፊት ደበደቧቸው፤ ከድብደባውም የተነሣ በእሳት የተጠበሱ እንጨት መሰሉ። ከድብደባው እብጠት የተነሣ የጉንጩ ስፋትና የከንፈሮቹ ሥርዓት (በእብጠት) ከአፍንጫው ጫፍ ጋራ እኩል ኾኑ። ዓይኑም ማየት አልቻለም። ብቻ ደሙ ከድንኳኑ በር እንደ ውሐ ይወርድ ነበረ። ... ሽማግሌው በርተሎሜዎስንም በጥፊ እንዲመቱት አዘዘ። “ከመጀመርያው ጥፊ ኃይለኛነት የተነሣ፣ የኋለኞቹን ልብም አሳልኳቸው” ይል ነበር። ከዚህ በኋላ፣ ሁሉንም ከሽማግሌው ጋራ እንዲገርፏቸው አዘዘ። ከንጉሡ ታላቅ ቁጣ የተነሣ እነዚያ በቀኙና በግራው ተቀምጠው የነበሩ ጳጳሳት መናገር አልቻሉም። ግን ለመግረፍ ካጋደሟቸው በኋላ እንዲተዋቸው አዘዘ። ቅዱሱንም ከወሰዱበት ቦታ አመጡት። (ሲያመጡት) አጐንብሶ ነበረ የሚሄደው፤ ምክንያቱም በጢሙ ላይ የወረደው የአፍንጫውና የአፉ ደም ሲረጋ እንደ ገመድ ሆኖ ሳይበጠስ ከልብሱ ጋር ተያይዞ ነበር። ሲመቱት ቆቡን ጥለዋት ስለነበረ ራሱ ራቂቱን ነበር፤ ... የደሙንም ገመድ ከጢሙ አስወገዱትለት። ዐይኑ ግን ጠፍቶም እንደሁ ወይም እንዳለ ለመረዳት አልቻሉም።” [14]
12.   በአጐዳ [ማለትም መላ አካላቸው ከመሬት በታች ቀብረው አንገታቸውን ብቻ በማስቀረት] እያንዳንዳቸውን ለማሰቃየት ከከተማና ከገጠር የታወቁ ፈረሰኞችን በመምረጥ በፈረስ ኰቴ ጨፈጨፏቸው፤  ከብቶችንም ነዱባቸው፤ በዚህ ኹኔታ አንድ መቶ ሰባት እስጢፋኖሳውያን ተጨፍጭፈዋል፤[15]
13.  ምላስና የሸኮናቸውንና የኹለቱ እግሮቻቸው ቋንጃ፣ ጆሮአቸውንም በአንድነት አስቆርጧል፤[16] እንዲቆረጥም አዋጅ አሳውጇል፤[17] በአንድ ቀንም የአንዲት ሴት መነኮሳዪይትን ጨምሮ የሃያ ዘጠኝ መነኮሳትን ምላሳቸውን አስቆርጧል፣ አፍንጫቸውን አስፎንኗል፣ ቋንጃዎቻቸውን አንድ በአንድ አስወጥቷል፤
14.  አፍንጫቸውን ፎንነው፣ ምላሳቸውን ቆርጠው፣ የሸኮና ቋንጃቸውንም አስቆርጠው በአህያ ከጫኗቸው በኋላ አህዮቹን አስቸኩለው ይነዱ ነበር፤[18]
15.  ቀኝና ግራ ጉንጫቸውን በ“ዘ” ቅርጽ፣ ግንባራቸውን፣ እጆቻቸውንም በምላጭ አስተልትሏል፤[19]
“... ሌሊቱን በሞላ በላያው በሚወርደው ዝናም፥ ከባሕሩ ማዕበል በሚመጣ የውሐ ውርጭ፥ በተኙበት ድንጋይ ቅዝቃዜ፥ ከግንባራቸው እና ከጒንጭ መተልተልና ከቋንጫ መቈረጥ በመጣ ቁስል በመቀጥቀጥ ሲያጥሩ አደሩ። ጊዜው ክረምት ስለነበረ በዚህ ዓይነት ሥቃይ ሲያጥሩ አደሩ። ...” [20]
16.  ከየገዳሞቻቸው እንዲሰደዱ አድርጓል፤[21] ንብረቶቻቸውን ኹሉም አስዘርፎባቸዋል፤ አቃጥሎባቸዋልም፤[22]
“እነሆ፥ ደቂቀ እስጢፋኖስ የተገኙበት ቤቱ ይዘረፍ፤ ገንዘቡ ይውደም፤ የቀበሌው ርስትም ለባዳ ይሁን። በጠዋትም ሆነ በምሽት ወደኛ ሲያመጧቸው እነርሱን ሳይገድሉ መሥዋዕት አያሳርጉ። ይኸንን ሳታደርጉ (ብታሳርጉ) መሥዋዕታችሁ የረከሰ ይሁን፤ እኔም ባላደርግ መንግሥታችን ለባዳ ይሁን።”[23]
17.  የወንዶቹን አባላቸውን አስቈርጧቸዋል፤[24]
18.  በጥፊ አስመትቷቸዋል፤ በብረት አንካሴና በጦር ሰውነታቸው እንዲጓጐጥ አድርጓል፤[25]
19.  ከነሕይወታቸው በአውሬ እንዲጐተቱ አስደርጓል፤[26]
20. አንገታቸው ከጉልበታቸው ጋር በቀበቶ እንዲታሠር አዝዟል፤[27]
“... በቀኙና በግራው ሰንሰለት፥ ባንገቱ ማነቆ አሰሩበት። ለልጆቹ የሞፈሮች እና የቀንበሮች ማነቆ አድርገውባቸው ሁለት ሁለቱን በአንድ ማነቆ አቆራኝተው እያስጨነቁ ወሰዷቸው። ደግሞ ደማቸውን በመንገድና በገበያ ያፈሱ ነበረ።”[28]
21.   በእርጥብ የበሬ ቆዳ አስደርጐ በተሸነቆረ ግንድ ውስጥ በማስገባት አሳስሯቸዋል፤[29]

22.  ማነቆና ቀንበር ከተደረገበት አንዱ እስጢፋኖሳዊ ሲደክም ሌላው የበረታው እንዲገባም አስደርጓል፤[30]
23. ልብሳቸውን፣ ቆባቸውን ጭምር በመግፈፍ እጅግ ከባድ ብርድ ባለበት ራቁታቸውን ረጅም ቀናት በማስቀመጥ አስፈጅቷቸዋል፤ አዝራት በተባለ ስፍራም ከብርዱ ከባድነት የተነሣ በአንድ ወቅት 98(ዘጠና ስምንት) እስጢፋኖሳውያን አልቀዋል፤[31]
  “ … ለዘለዓለም ሕይወት ነዋሪ ፍሬ እንዲያፈሩና እንዲጥሉ በፈቃዱ ሥቃዩን ለመሸከም ልዑል (ጌታ) ጠርቷቸዋል፤ ሰብስቧቸዋልምና። እዚያ ከፍ ባለ ጣር በብዙ ጻማ፥ ምግብ ከማጣት በሚመጣ አስጨናቂ ድካም ኖሩ። ቍርበትና ምንጣፍ ከሌለበት አሸዋ መሬት ላይ በተኙበት ከቀኝ ወደ ግራ፥ (ከግራ ወደ ቀኝ) ይንቀሳቀሳሉ እንጂ ከሰውነታቸው መመንመን የተነሣ መቆም መቀመጥ አልቻሉም። እንደ ድርቅ ዘመን መሎክ ጠወለጉ። መልካቸው ተለወጠ፤ ኀይላቸው ደከመ። ሁሉም በራሱ የደረሰበትን ይታገሣል፥ የሥጋን ጭንቅ ይቅር ይላል፤ ቍስላቸውን ለማጠብም ሆነ ለጥማቸው እንዲጠጡም የሚረዳቸው አልነበረም። ብቻ አንዳንድ ከነሱ የበረታ ወደ ባሕሩ ተጐትቶ ይሄድና በአንገቱ ቅል አንጠልጥሎ ለወንድሞቹ ውሐ ያመጣና ቁስላቸውን ያጥብላቸዋል፥ ይጠጡለታልም። ከአስኬማቸው ብጣሽ ጨርቅ በቀር ምንጣፍ፥ ሽፋን፥ ቆብ ከሌለበት መሬትና ትቢያ ላይ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይተኛሉ። (ብጣሿ ጨርቅም ብትሆን) የሥቃያቸውን ደም ጠጥታ ነበረ። …”[32]
24. ለአረሚ እስላም አሳልፎ በክፋት ልብ በመስጠት፣ በተራራ ላይ እንዲከማቹና ምንም ዓይነት ምግብ እንዳያገኙ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ፣ በረሃብ ጠውልገው እንዲያልቁ አድርጓቸዋል፤ በውሐ ጥም አስፈጅቷቸዋል፤[33]
25. ከበቅሎና ከአህያ ጋጥ ጭቃ ላይ አስጥሏቸዋል፤ [34]
26. በሞላ ወንዝ ውስጥ አስወርውሯቸዋል፤ [35]
27. ሙዓለ መሀፒል ከሚባል ዓለት ድንጋይ ላይ አስጥሏቸዋል [አስፈጥፍጧቸዋል]፤ [36]
28. መሬት ለመሬት በብረት ሰንሰለትና በገመድ ሰውነታቸው እስኪገሸላለጥ አስጎትቷቸዋል፤[37]
29.  እጅና እግራቸውን አስቆርጧል፤[38]
“ ... በማግሥቱ በጠዋት በጋላቢ ፈረስ የተቀመጠ (መልእክተኛ) እንዲህ ሲል ላከ፤ “እሺ ይሉህ እንደሆነ ለንጉሥ ስገዱ በላቸው። እንቢ ካሉህ እግራቸውንና እጃቸውን እዚያው ቁረጣቸው።” (መልእክተኛው) ትእዛዝ ተቀብሎ ወጣ። በጋላቢ ፈረስ ሄዶ ቅዱሳኑ ካደሩበት ደረሰ። ... ከወታደሮቹ አንዱ ሰይፉን ከፍ አድርጎ እጆቹንና እግሮቹን ባንዴ ቈረጣቸው። ከዚያ፥ ያ ወንድም፥ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ለዓለም ስቡሕ ነው፥ ልዑልም ነው” አለ። ... አንዳንዶቹ ከመጽሐፍ (እየጠቀሱ) ይዘምሩ ነበረ። ሁሉም መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለው ተናገረ።
ከዚያ፥ በየተራቸው ወደ ሰያፊው ወረዱ። ባለሰይፉ ሰይፉን ከለከለ፤ “ሰይፌን አታደንዝብኝ” አለ። ከዚያ፥ የዚያን አገር ሰዎች፥ “ከየቤታችሁ ቢላዋ አምጡ” አላቸው። ቅዱሳኑ እንዳይጐዷቸው ምላጫቸውን ሰጡ። ሰዎቹም ቢላዋ አመጡ፤ በዚያ ቢላዋና በምላጭ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቈረጧቸው። ...”[39]
30. እጅና እግራቸው ተቆርጦ የተረፉትን በደብረ ብርሃን ዙርያ በሚገኙ እጅግ ውርጭና ቆፈናም ተራራዎች ላይ እንዲቀመጡ አዝዟል፤ የተቀሩትንም ቈላ አውርዶ በሐሩርና በሙቀቱ ንዳድ እንዲጠበሱ ያስደርጋቸውም ነበር፤[40]
31.  በሕይወት ሳሉ እንደተቀበረ በድን በዝግ ቤት ውስጥ አስቀብሯቸዋል፤ [41]
32. ለወራት ያህል በእግር ብረትና በተበሳ ግንድ አስሯቸዋል፣ በተደጋጋሚም ምንም ብርሃን በማይገባበት በጨለማ ቤት ውስጥ እጅና እግራቸውን በማሰር አግዟቸዋል፤[42]
33. እነርሱ በእስር ሳሉ የሚጠይቋቸውን፣ በምግብና በመጠጥ የሚረዷቸውንና የሚተባበሯቸውን ኹሉ ያስር ያስገርፍም ነበር።[43]
  የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን መከራ ይህ ብቻ አይደለም፤ ቀጣዩን በሚቀጥለው ክፍል እናቀርባለን። ይህን ስንናገር ወንጌልና የእግዚአብሔር እውነትን መመስከር ከዚህም በላይ ዋጋ እንደ ሚጠይቅ ባለመዘንጋት ነው። እንግዲህ እነዳንኤል ክብረት ጥረትና “አዲስ ታሪክ ፍብረካ የተያያዙት” ይህን ሕያው እውነት ለመቅበርና ለማክፋፋት ነው። ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር አብ ስለልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ በሕይወታቸው ተወራርደው የመሰከሩለትን ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ሥራቸውና የወንጌል ምስክርነታቸው ከተቀበረበት እንዲወጣ አድርጓል።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በጸጋው በኹለንተናችን እንድንገዛለት፤  በነፍሳችን ተወራርደን እንድናመልከው ይርዳን፤ አሜን።
ይቀጥላል …



[1] የኢትዮጵያ ዓመታዊ ታሪክ መጽሔት 4ኛ እትም፤ 1954፤ ገጽ 79-87፡፡
[2]  ተአምረ ማርያም፤ ግእዝና አማርኛ፤ 111 ተአምራትን የያዘ፤ 1989 ዓ.ም 3እትም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ገጽ.94-101፤ ከቁ.1-76። የኢትዪጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ 1986 ዓ.ም 2 እትም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ፤ ገጽ.49። ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 158ኤልያስ ግርማ(መሪጌታ) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጎ ፤ 2000 ዓ.ም ፤ ማተሚያ ቤቱ ያልጠቀሰ
[3] ዝኒ ከማሁ፤ ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር፡፡ ምንኩስና በኢትዮጲያ ዛሬና ትናንትና፤ 2000 ዓ.ም ፤ አሳታሚ አልተጠቀሰም፤
[4] ዝኒ ከማሁ፣ ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤  ገጽ ገጽ 129፣ 156-157፣ 171-172፣ 215፣ 218
[5] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 133
[6] ዝኒ ከማሁ ገጽ 133 
[7] ዝኒ ከማሁ ገጽ  133
[8] ዝኒ ከማሁ ገጽ  191
[9] ዝኒ ከማሁ ገጽ 198
[10] ዝኒ ከማሁ ገጽ 201
[11] ዝኒ ከማሁ ገጽ 95፣ 108፣ 175
[12] ዝኒ ከማሁ ገጽ  171፣ 211፣ 214
[13] ዝኒ ከማሁ ገጽ 95፣ 107፣ 108፣ 111፣ 120፣ 122-123፣ 129፣ 137፣ 144፣ 146፣ 148፣ 153፣ 174፣ 190፣ 206
[14] ዝኒ ከማሁ ገጽ  103-105፣ ገድለ አቡነ እስጢፋኖስ፤ 1996 ዓ.ም፤ አሳታሚ አሲራ መቲራ ገዳም፤ ገጽ 160-161
[15] ግርማ ዘውዴ፤ ኢትዮጲስ አራተኛ እትም፤ የካቲት 1985  ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ፡፡ ገጽ 90
[16] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤  160፣ 177
[17] ዝኒ ከማሁ ገጽ  170
[18] ዝኒ ከማሁ ገጽ 174
[19] ዝኒ ከማሁ ገጽ 110፣ 121፣ 158፣ 159
[20] ዝኒ ከማሁ ገጽ  160፣ 197
[21] ዝኒ ከማሁ ገጽ 233
[22] ዝኒ ከማሁ ገጽ  111፣ 126፣ 148፣ 175፣ 190፣ 197
[23] ዝኒ ከማሁ ገጽ  175
[24] ዝኒ ከማሁ ገጽ 174
[25] ዝኒ ከማሁ ገጽ 103፣ 133፣ 150፣ 211፣ 214
[26] ዝኒ ከማሁ ገጽ 172
[27] ዝኒ ከማሁ ገጽ 171
[28] ዝኒ ከማሁ ገጽ ገጽ 128፣ 143፣ 152
[29] ዝኒ ከማሁ ገጽ 190
[30] ዝኒ ከማሁ ገጽ  138፣ 170፣ 173
[31] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤  ገጽ 145፣ 146፣ 154 ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጐ፤ ገጽ 140
[32] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤  ገጽ 160፣ 190
[33] ዝኒ ከማሁ ገጽ ገጽ.74፣ 143
[34] ዝኒ ከማሁ ገጽ 143
[35] ዝኒ ከማሁ ገጽ 143
[36] ዝኒ ከማሁ ገጽ 160
[37] ዝኒ ከማሁ ገጽ 143፣ 195፣ 208
[38] ዝኒ ከማሁ ገጽ 171፣ 172፣ 176፣ 177፣ 193፣ 195
[39] ዝኒ ከማሁ ገጽ 193
[40] ዝኒ ከማሁ ገጽ 206
[41] ዝኒ ከማሁ ገጽ 74
[42] ዝኒ ከማሁ ገጽ 74፣ 105፣ 111፣ 130፣ 131፣ 133፣ 138፣ 185
[43] ዝኒ ከማሁ ገጽ 120፣ 145፣ 192፣ 205-206

28 comments:

  1. ወዳጄ መጀመሪያ ዘርያዕቆብን ከመኮነን በፊት እነርሱ መገኘት ከሌለባቸው ቦታ ለምን ተገኙ ? ምንግዜም መረሳት የሌለበት ነገር ልንገርህ መስቀል ስር የተገኘ ሰይጣን ምን ይገጥመዋል ብለህ ማሰብ አለብህ መመንፈቅ ይቻላል ግን ከቤተ ክርስቲያን ወጥቶ ነው መመንፈቅ የሚቻለው ቤተክርስቲያን ተቀምጦ አይሆንም እዚያ ከተገኙ ግን የሚመጣውን በፀጋ መቀበል ያስፈልጋን ፡፡ለማንኛውም ይህን መጽሐፍ የጻፉትም ሆነ አሁን ለዚህ ግብአት የተጠቀሙት አካላት በምንፍቅናው አለም ያሉና ቤተ ክርስትያንን ለመውቀስ የሚዳዱ አንድም እውነት አንድም ዕውቀት አንድም ብቃት የሌለው ሰው ነውና እኛም ሰምተን ጆሮ ዳባ አንብበንም አንዳልተጻፈ አልፈነዋል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Dear to say some thing about Dekike Estifanos first you have to read and know in detail...if you Know Aba Estifanos were the Founder of 37 monastries including Gundagunde.

      Delete
    2. መጽሐፉን አላነበብከውም

      Delete
  2. ስለ መናፍቃን የሚያመው መናፍቅ ብቻ ነው ከፈለክ መከተል መብትህ ነው ግን በስመ ዲያቆን አት ነግድ አቤኔዘር

    ReplyDelete
  3. ስለ መናፍቃን የሚያመው መናፍቅ ብቻ ነው ከፈለክ መከተል መብትህ ነው ግን በስመ ዲያቆን አት ነግድ አቤኔዘር

    ReplyDelete
  4. ምነው ታዴ ቤተክርስቲያን አንተንም ልጅ ብላኮ ስቀልብ ኖራለች ይሄኔ

    ReplyDelete
  5. "አሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ" ክርስቲያን መስሎ ክርስትናን ለመውጋት መጠጋት እንዳይሆንብን ትርፉ ትዝብት ነው። ክፎዎቹና ነፍሰ በላዎቹ እነደቀእስጢፋንጂ በእውነቱ ንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብና የዚያን ጊዜ አገልጋዮች ሊወነጀሉ አይገባም ነበር ። ነገር ግን አሁንም የደቀእስጢፋ ውራጆች ስላላችሁ ሕዝቡን ለማሳሳት የማታነሡት ነገር የማትቆፍሩት ጉድጓድ የለም ። ልቦና ይስጣችሁ ። አሁንም ለዘለዓለም የተዋህዶ አንበሳ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ ፍፁም የሆነ በተዋህዶ የከበረ ሕይወትና አዳኛችን እንጂ የነሉተር ጭንቅላት የሠይጣን ምክር የፈለሠፈው ሌላ አማላጅ ቅብርጥስዬ ቅብርጥስዬ አይደለም ።

    ReplyDelete
  6. "አሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ" ክርስቲያን መስሎ ክርስትናን ለመውጋት መጠጋት እንዳይሆንብን ትርፉ ትዝብት ነው። ክፎዎቹና ነፍሰ በላዎቹ እነደቀእስጢፋንጂ በእውነቱ ንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብና የዚያን ጊዜ አገልጋዮች ሊወነጀሉ አይገባም ነበር ። ነገር ግን አሁንም የደቀእስጢፋ ውራጆች ስላላችሁ ሕዝቡን ለማሳሳት የማታነሡት ነገር የማትቆፍሩት ጉድጓድ የለም ። ልቦና ይስጣችሁ ። አሁንም ለዘለዓለም የተዋህዶ አንበሳ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ ፍፁም የሆነ በተዋህዶ የከበረ ሕይወትና አዳኛችን እንጂ የነሉተር ጭንቅላት የሠይጣን ምክር የፈለሠፈው ሌላ አማላጅ ቅብርጥስዬ ቅብርጥስዬ አይደለም ።

    ReplyDelete
  7. this is false accusation Zera Yakoblivein the era of dictatorship there is no so called democracy so what he can do?? u idiot!

    ReplyDelete
  8. እኔ ምለው ድንግል ማርያምን የጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እናት ለመቃወምና ላለማክበር ለዘመናት በጭፍኑ ብትሉት ብትሉት አልሄን ቢላችሁ ስሟን ያከበሯትንና ስለግብሯ የተቀኙትን መንቀፍ ስራ አደረጋችሁት በበርም መጣችሁ በመስኮት ሴይጣ ተንጫጫም ተረበሸም የሚያመሰግናት የሚያከብራት ብፅዕትም የሚላት ትውልድ ነው።

    ReplyDelete
  9. እኔ ምለው ድንግል ማርያምን የጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እናት ለመቃወምና ላለማክበር ለዘመናት በጭፍኑ ብትሉት ብትሉት አልሄን ቢላችሁ ስሟን ያከበሯትንና ስለግብሯ የተቀኙትን መንቀፍ ስራ አደረጋችሁት በበርም መጣችሁ በመስኮት ሴይጣ ተንጫጫም ተረበሸም የሚያመሰግናት የሚያከብራት ብፅዕትም የሚላት ትውልድ ነው።

    ReplyDelete
  10. ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ለስዕል ና ለንጉስ አንሰግድም አሉ እንጂ እንደአንተ እና እንደመሰሎችህ ኢየሱስ አማላጅ አላሉም ዲያቆን ዳንኤል የናንተ ሸፍጥ ስለገባው እንቅጩ ነው የተናገረው በደቂቅ እስጢፋኖሳውያን ላይ የተፈፀመው ድርጊት አግባብ እንዳልሆነ ሲገልፅማ ሰማህትነትን ተቀበሉ ብሏል ዳንሄል ምኑ ነው የክፋት ሸፍጥ ያሰኘክ

    ReplyDelete
  11. Mndnew mtaweraw? menafk neh ante rasih

    ReplyDelete
  12. እንናት ነጣቂ ተኩላዎች ጥፋ ከዚ ሰይጣን ።እሄን ወር ሰሞን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ላይ በተለያየ አምድ ተደራጅታችው የጀመራችውት የስም ማጥፋት ለማንቋሸሽ የከፈታችውት ዘመቻ ምመኑ ያውቃል ።በናንተ የተንኮል የምቀኝነት የጥላቻ የተንሸዋረረ አመለካከት የሚሰናከል ሰውየለም እናንተ የቅዱሱን ሰማእት ስም ይዞ እርኩስ ተግባር የሚሰራ ማህበር የለም በቅዱሳን ስም አትነግዱ ውጡ ቤቴ የጸሎት ቤት እንጅ የወንበዴዎች ዋሻ አይደለም ነው ያለው እናም እናንተ ጭብል የለበሳችው አሪሶዊያን ተሀድሶ መናፍቅ ቤተክርስቲያናችንን እና ልጆቹዋን ለቀቅ አድርጉ ።ለጮኸ ውሻ ሁሉ ድንጋይ (መልስ) አይወረወርም አይሰጥም ።ተኩላ ሁላ የሰይጣን የጭንቅ ልጆች ለመከፈል የተፈጠራችው ስጋ ለባሽ አጋንንት ይሉሀል እናንተና መሰሎቻችው ናችው ።እረፉ ተነቅቶባችዋል እፉኝት ልጆች ሁላ

    ReplyDelete
  13. አስመሳዩ መናፍቅ ተኩላው ተነቅቶብሃል ከዳኒ ላይ ወረድ በል

    ReplyDelete
  14. ዳንኤል እውነተኞቹን ቅዱሳንንና ሰማዕታትን ንቋል ስትል ትንሽ አታፍርም???የምር ታሳፍራለህ

    ReplyDelete
  15. እንናት ነጣቂ ተኩላዎች ጥፋ ከዚ ሰይጣን ።እሄን ወር ሰሞን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ላይ በተለያየ አምድ ተደራጅታችው የጀመራችውት የስም ማጥፋት ለማንቋሸሽ የከፈታችውት ዘመቻ ምመኑ ያውቃል ።በናንተ የተንኮል የምቀኝነት የጥላቻ የተንሸዋረረ አመለካከት የሚሰናከል ሰውየለም እናንተ የቅዱሱን ሰማእት ስም ይዞ እርኩስ ተግባር የሚሰራ ማህበር የለም በቅዱሳን ስም አትነግዱ ውጡ ቤቴ የጸሎት ቤት እንጅ የወንበዴዎች ዋሻ አይደለም ነው ያለው እናም እናንተ ጭብል የለበሳችው አሪሶዊያን ተሀድሶ መናፍቅ ቤተክርስቲያናችንን እና ልጆቹዋን ለቀቅ አድርጉ ።ለጮኸ ውሻ ሁሉ ድንጋይ (መልስ) አይወረወርም አይሰጥም ።ተኩላ ሁላ የሰይጣን የጭንቅ ልጆች ለመከፈል የተፈጠራችው ስጋ ለባሽ አጋንንት ይሉሀል እናንተና መሰሎቻችው ናችው ።እረፉ ተነቅቶባችዋል እፉኝት ልጆች ሁላ

    ReplyDelete
  16. ደቂቀ እስጢፋኖስ ያውኮ ሌላ ገጽ ያለው መናፍቅ ማለት ነው

    ReplyDelete
  17. May God bless you abundantly!

    ReplyDelete
  18. May God bless you abundantly!

    ReplyDelete
  19. አግዝብሕርወደመነገዱየመለሳቻህ

    ReplyDelete
  20. AMEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEEN
    AMEEEEEEEEEEEEEEEEEEEN GETA ZEMANIHNNNNNNNNN YIBARKI TABARAKKKKKKKKKKK 👏👏👏👏👏👏👏👏👏💕💜

    ReplyDelete
  21. አቤኔዘር ይሉ ደንቆሮ ተሃድሶ ዝም ብለክ ይሄን ነገር ደጋግመ ስለ ፖሰትክ እውነት አይሆንም።

    ReplyDelete
  22. Behiwote yemitelaw neger binor endezih ayinet asmesayinet new. Betelyi degmo slemayawukut neger eyezebarku yemiyasmeslu sewochn nebse ttelalech.

    ReplyDelete
  23. ከሰይጣን ጋር አንዲትን ስምምነት አደአግሁ፡፡ ሁሌም እንዲጠላኝ ሁሌም እንድጠላው፡፡ እኔ አናት አናቱን ስረግጠው፡ እሱ ሰኮናዬን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው፡፡

    ReplyDelete
  24. እኚህ አፄ ክፉ መንፈስ ተቆጣጥሯቸው ነበር መቼም ጤነኛ ሰው ይህንን አያደርግም

    ReplyDelete
  25. ይህ እዉነት የደቂቀ የደቂቀ አስጢፋኖስ መነኮሳት ከአፄ ዘርአያቆብ ጋር ያላስማሟቸውና በአፄው እንዲጠፉ ያስወሰኑባቸው የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፤
     “ከፈጣሪ ውጪ ለማንም ማጎንበስ፣ መስገድ ስሕተት እንደሆነ” ያምኑ፣ ያስተምሩ ነበር፤ ለንጉሱ ለማገንበስም ፍቃደኛ አልነበሩም፤ ማርያምም ሆነ ሌሎች ቅዱሳት፣ መላዕክትም ቢሆኑ ሊከበሩ ሊዘከሩ እንጂ ሊሰገድላቸው እንደማይገባ ያስተምሩ ነበር፤
     “ሐይማኖትና መንግስት መለያየት አለባቸው” ብለው ያምኑ ስለነበር፤ በተለይም አፄ ዘርአያቆብና ከፊት የመጡ ነገስታት ከአንዳንድ ሐይማኖቱ መሪዎች ጋር በመሻረክ (ለአብነት ከአቡነ ተክለሃይማኖት ጋር) ቤተ-ክርስትያኒቱ የንጉሱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንድትሆን፣ ቤተክርስትያንና ገደማትም ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያገኙ የፈፀሙት ሻጥር (“ሲሶ ለነጋሽ፣ ሲሶ ለአራሽ፣ ሲሶ ለቀዳሽ” የሚለውን አዋጅ) በፅኑ ተቃወሙ፣ ሑሉም ሰርቶ ጥሮ-ግሮ መብላት እንዳለበት መፅሐፍ እንደሚስተምር ተከራከሩ፤ በዚህም ንጉሱና ጥቅም ፈላጊ የሐይማኖት አባቶች ጥርስ ነከሱባቸው፤
     “ለእንጨት መስቀልና ለስዕል ማጎንበስ የለብንም” ብለው ያምኑ ስለነበር፤ - “የአፄ ዘርአ የዕቆብ ደብተራዎች የፃፉትን ተአምረ-ማርያም ብዙ እንከን ያለበትና ተቀባይነት የሌለው ፀረ-ክርስትና ነው” ብለው ያምኑ ስለነበር፤ - ደቂቀ እስጢፋኖሶች ከሀይማኖታዊ ምጥቀት በተጨማሪ ከፍተኛ የሳይንስ እውቀትም አዳብረው ስለነበር፤
    ብዙዎቹ እነዚሁ የደቂቀ አስጢፋኖስ ሐሳቦች ማርቲን ሉተር ኪንግ ከ30 ዐመት በኃላ ተነስቶ ከዐለም አስተጋብቷቸዋል፡፡ በፕሮቴስታኒዝምና በደቂቀ እስጢፋኖስ መካከል መሰረታዊ የነገረ-መለኮት የትርጓሜ ልዩነት እንዳለ ግን ሳንዘነጋ ነው፡፤
     ማርያምም ሆነ ሌሎች ቅዱሳት፣ መላዕክትም
    ይሄ የእዉነት የኦርቶዶክስ እምነት ነዉ፡ እመኣምላክ የፀጋ ስግደት ይገባታል ሌሎች ቅዱሳን ደግሞ የኣክብሮት ስግደት የገባቸዋል፡፡
     “የአፄ ዘርአ የዕቆብ ደብተራዎች የፃፉትን ተአምረ-ማርያም ብዙ እንከን ያለበትና ተቀባይነት የሌለው ፀረ-ክርስትና ነው” ብለው ያምኑ ነበር፤
    ታኣምረ ማርያም የፃፈዉ ማን ነዉ፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተዉ የፃፉት ኣባቶች ኣይደሉም ወይ; እንከን ካለበትስ ለምን እዉነተኛዉ ይሄ ነዉ ብለዉ ኣይሞጉቱም; ፀረ ክርስትና ከሆነ ለምን እነርሱ አየስተካክልቱም፡
     “ለእንጨት መስቀልና ለስዕል ማጎንበስ የለብንም” ብለው ያምኑ ስለነበር፤
    ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ኣሳነሱት ይሄ እዉነት ነዉ; ይገባዋል ወይ; ሰይጣን የተሸነፈበትና የተቀጠቀጠበት ቅዱስ መስቀል ማናቃሸሽ ይገባል ወይ;
    ልቦና ይስጠን እዉነቱን እንድናዉቅ የድንግል ማርያም ልጅ ፈጣሪ እየሱስ ክርስቶስ ይርዳን ኣሜን፤፤

    ReplyDelete
  26. በስመአብ! ምናለ በሐይማኖት እና በህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር ይህን ያህል ክምትደክም ጊዜሀን ለሚጠቅም ነገር ብታውለው?

    ReplyDelete