Tuesday 18 April 2017

‘የሱስን ልበሱ

PLease read in PDF


ድሪት አትደርቱ፣ መጣፍያ አትለጥፉ፤
በአዲሱ ልብስ ላይ፣ ያረጀውን አትስፉ፤
አሮጌ አሮጌ ነው፣ መቦጨቁ ላይቀር፤

ከኃጢአት እራፊ ጋር፣ ይቅር መደራደር!
ይቅር ከአሮጌው ጋር፣ የእሹሩሩ ኑሮ፤
በኢየሱስ መውጣት ነው፣ ጨክኖ ተጋድሎ፡፡
የኋለኛው አዳም፣ በእናንተ እንዲሠራ፤
ብርሃናችሁ ደምቆ፣ በሥራ እንዲያበራ፤
የአሮጌውን ሰው ልብስ፣ ጥላችሁ ተነሡ፤
ከቀጭን ተልባ እግር፣ እጅግ ያማረውን፣ ‘የሱስን ልበሱ!

3 comments:

  1. የኋለኛው አዳም፣ በእናንተ እንዲሠራ፤
    ብርሃናችሁ ደምቆ፣ በሥራ እንዲያበራ፤
    የአሮጌውን ሰው ልብስ፣ ጥላችሁ ተነሡ፤
    ከቀጭን ተልባ እግር፣ እጅግ ያማረውን፣ ‘የሱስን ልበሱ!
    wow best aeticle

    ReplyDelete
  2. የኋለኛው አዳም፣ በእናንተ እንዲሠራ፤
    ብርሃናችሁ ደምቆ፣ በሥራ እንዲያበራ፤
    የአሮጌውን ሰው ልብስ፣ ጥላችሁ ተነሡ፤
    ከቀጭን ተልባ እግር፣ እጅግ ያማረውን፣ ‘የሱስን ልበሱ!
    tebarek

    ReplyDelete