Friday 31 October 2014

ተጠርተናል ጥሪ


                               Please read in PDF
                                     
እግዚአብሔር አዳምን በመልኩ ሲፈጥረው፤
አዳም በራሱ መልክ ቃየልን ወለደው፤

ከዚያኔ ጀምሮ ውልደቱ ሲጨምር፤
እየሰፋ ሄደ ርኩሰትና ነውር!

ባʻንዱ ባʻዳም ምክንያት ምድር ተረገመች፤
በሞት በመቃብር ጨለማ ተዋጠች፤
ከዚህ የተነሳ …
የሰው ልጅ የመርገም አክሊል በመድፋቱ፤
አንድ ልጅ ተላከ ከሰማይ አባቱ … ፤

አንዱ ስለማርከስ ለአለሙ ሲበቃ፤
ከወንድ ዘር ያይደል ከሴት ዘር በሥጋ፤
ሊያድንና ሊቤዥ አንድ ጌታ መጣ፡፡

ስለዚህም እኛ…
ከሁለተኛው አዳም ትውልድ ለመቆጠር፤
ተጠርተናል ጥሪ በልጅነት ሥልጣን -

                            በማመን እንድʻኖር፡፡ 

No comments:

Post a Comment