Wednesday 19 February 2014

የማይቆም ድምጽ አለ !



ተቻኮልና ሂድ
  አትቁም ከመንገድ
  ደፍረህ ተናገረው
  ጩህና ስብከው
         አትዘግይ ወደኋላ
         ፈልቶ በዝቶ ተኩላ
         አትተኛ ንቃ በክርስቶስ ብርሐን
         ጮኸህ ተናገረው የወንጌሉን መዳን

የማይሰለች ድምጽ  ዕረፍት የሚነሳ
እንድታጠቅ ትጥቁን የእውነትን ጋሻ
ተነስ ፍጠን ብሎ የሚጮህ ቃል አለ
እሳት የእሳት ላንቃ ፍህም የመሰለ፡፡
          ነውር ምድርን አካሎ
           ኃጢአት ሁሉን ከድኖ
           እያየህ ስለምን ዝምታን መርጠሀል
           እያለ ወንጌሉ ይቀሰቅሰኛል
ጌታ ሆይ አበርታኝ አስጨክነኝ ዛሬ
መድኃኒቴ 'ባክህ ኃይልን ስጠኝ አንዴ
እንደሶምሶን ብዙ ጠላትን ፈጅቼ
ይድመቅልኝ ክብሬ ክብርህን አይቼ
                እውነትህን ሰብኬ!!!

No comments:

Post a Comment