Friday 3 May 2013

በእገሌ ቤት ውስጥ

Please read in PDf

የሲናን በረሀ የቃዴስ
በእሳትና መብረቅ በማረስ
እልፍ ነፍሳትን በቁጣ አቅልጦ
ምርጡን ለራሱ አብልጦ መርጦ
በእንቅጥቅጥ ፍርሀት               
በህግ ስርዓት
ልብን እያራደ
ብርቱን እየናደ
ያ የብሉይ መስዋዕት
የጊዜው ፍትሀት
በአንድ ማንነቱ በውል ባልታወቀ
(እ)ገሌ በተባለ
ያ አስፈሪው ሥርዓት በድንገት አለፈ፡፡
        ለኃጢአተኞች እረፍት
        መጽናናትና ህይወት
        አንዴ ተሰውቶ የዘለዓለም ፈውስ
        መንፃትና ስርየት ፍጹሙን መቀደስ
        በእምነት ህይወትን ዘወትር እያደለ
        በምሴተ-ሀሙስ በእገሌ ቤት ውስጥ የኪዳኑ መስዋዕት እንዲህ ተቋቋመ።
ትንሹን አክባሪ
ያልታወቀን ጠሪ
በምሴተ-ሀሙስ ድግሱን ደግሶ
ፍጥረትን ጋበዘ ሥጋ ደሙን ቆርሶ፡፡

No comments:

Post a Comment