Friday 10 May 2013

አትፈር አትፍራ

Please read in PDf

አታመንታ ቀኝ ግራ
በሞተልህ ልትኮራ
ክርስቶስን ልትጠራ
አትደንግጥ አትሸበር
ተወልደሀልና ከማይጠፋ ዘር፡፡

ምንድር ነው መርበትበት?
ጭንቀትና ሥጋት?
አይከፈል አቅልህ ፅና በክንዶቹ
ልብህ አይናወጥ ታይተሃል በአይኖቹ፡፡
በመንፈስ ተቃጥለህ በትክክል ጥራው
ምስጋና አምልኮ ለ‘ርሱ ብቻ ስጠው 
 መስክርለት በሕይወት መንፈሱ ካንተ ነው
ማንም አይችልህም ተዋጊህ እርሱ ነው
የሌጌዎን ጭፍራ ሞገዱን አትፍራ
ለእርሱ በመኖርህ መቶ እጥፍ እንጂ የለውም ኪሣራ
ከፍ አድርገው ስሙን ጮኽህ ተናገረው
ያለ የነበረ የሚኖር ሕያው ነው
አትፍራ አትደንግጥ ሩጥ በብዙ ትምክህት
አይቀርቡም ወዳንተ የአጋንንት ሠራዊት
ከብረት ጋሻ ይልቅ ይመክታል ስሙ
ተግተህ ተዋጋ እንጂ አታስብ ለድሉ
በክብር መሞቱ ሞገስ ነው አትፍራ
ነፍስ የሚቀጣውን እርሱን ብቻ ፍራ
ተጓደድ በስሙ አትታወክ በርታ
የቆምክባት ዓለት ነውና አለኝታ
አትፈር አትፍራ ኢየሱስ ነው ጌታ፡፡  



1 comment: