Friday 24 May 2013

እውነተኛ አፍቃሪ

Please read in PDF

አፍላ አይከጅልም 
ቆንጆም አይሰርቀውም
እንደባህር ኩበት አይንቀዋለልም
በሄደበት ሁሉ ቢጥዱት አይሞቅም
እውነት ናት መርከቡ
ፍቅር ነው ቀለቡ
እንደልቡ አይደለም ቁጥብ ነው መንፈሱ
እውነተኛ አፍቃሪ መታመን ነው ልብሱ
ምን ይሉኝ አያውቅም ቁርጥ ነው አቋሙ
አፍቃሪ ያፈቅራል ቢቀር እንኳ ጥቅሙ
በሰው ጫካ ሆኖ ሰው ተርቦ ይጠማል
ላየው ነገር ሁሉ መች ቀልጦ ይቀራል
እውነተኛ አፍቃሪ ላመነው ወዳጁ ሞትን እንኳ ያያል፡፡

No comments:

Post a Comment