ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ብዙ አመንትቻለኹ፤ ለተሐድሶ አገልግሎት ከማይመቹ አካሄዶች መካከል የነትዝታውን የሚመስል አስከፊ መንገድ የለም፤ እነ ትዝታው ከ“አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል” ውስጥ ራሳቸውን አዳብለዋል፤ ይኹንና ካውንስሉ በውስጡ፣ የክርስቶስን ርቱዕ ትምህርት፣ ሕይወትና ሥራ የማይቀበሉ ያሉትን ያህል፣ እነ ትዝታውም እውነተኛ የወንጌላውያን አማኞች እንዳልኾኑ የሚያሳዩ አያሌ ምልክቶች አሉ።
ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ብዙ አመንትቻለኹ፤ ለተሐድሶ አገልግሎት ከማይመቹ አካሄዶች መካከል የነትዝታውን የሚመስል አስከፊ መንገድ የለም፤ እነ ትዝታው ከ“አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል” ውስጥ ራሳቸውን አዳብለዋል፤ ይኹንና ካውንስሉ በውስጡ፣ የክርስቶስን ርቱዕ ትምህርት፣ ሕይወትና ሥራ የማይቀበሉ ያሉትን ያህል፣ እነ ትዝታውም እውነተኛ የወንጌላውያን አማኞች እንዳልኾኑ የሚያሳዩ አያሌ ምልክቶች አሉ።
በዚህ ባለንበት "የክርስትና ዐውድ" ሰዎች "ወንጌል ተረዳን" ሲሉ፣ ከአንድ ኅብረት ወደ ሌላ ኅብረት "ቀለል ባለ መንገድ ሲሸጋገሩ" ማየት የተለመደ ኾኖአል። ርግብ ቤቷ ጨርሶ እስካልፈረሰና ጫጩቶቿን እስካልገደሉባት ድረስ ስላባረሯት፣ ስለመቷት ... ብቻ ከጎጆዋ አትወጣም ተብሎ በሚነገረው የኦርቶዶክስ ማኅበረ ሰብ ውስጥ የኖረውም ኾነ፣ ከኅብረት መውጣት "የዓሳ ከባሕር የመውጣት ያህል" ከባድ ነው በሚለው የወንጌላውያን ማኅበረ ሰብ ሰዎች ይወጣሉ፤ ይፈልሳሉም።
በሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን
ከበርካታ ወራት በፊት በተንቀሳቃሽ ስልኬ በተላከልኝ አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) ላይ አንድ “ፍተላ” ብጤ አነበብኩ፡፡ “ፍተላው” የሚያስፈግግ ነገር ነበረው፡፡ ኾኖም ግን ድንጋጤው በቅጡ ነዝሮኛል፡፡ ነገርዬው እንደሚለው፣ አንድ የሃይማኖት አባት “አንድ ወርኀዊ በዓል በነባሮቹ ላይ አከሉ፡፡ ይኸውም፤ በ1 ልደታ፣… በ3 በኣታ፣… በ5 አቦዬ፣ በ6 ኢየሱስ፣ በ7 ሥላሴ፣ በ8 ቢዮንሴ” ይላል፡፡ ይህ ሥላቅ ያላስፈገገኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ ሁለተኛው፣ የሕዝብህን አለቃ አታንጓጥጥ (ዘዳ. 22÷28፤ የሐዋ. 23÷5) የሚለውን ቅዱስ መርሕ ስለጣሰ ነው፡፡ አንደኛውንና ዋነኛውን ምክንያት ደግሞ በዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ አመላክታለሁ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ በፍጥረት መጀመሪያ ያስቀመጠው እውነት፣ “እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤
እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ።” (ዘፍ. 1፥31) የሚል ነው። ስለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ በመልካም ነገር ደስተኞች ኾነን
እንድንኖር ነው። ነገር ግን በብዙ ጥንዶች መካከል፣ ይህ መልካም ደስታ ጨንግፎና መክኖ ይስተዋላል። በተለይም ደግሞ በዚህ
ዘመን ፍቺና “ከፍቺ በኋላ ያለ የብቻ እናትነት” እንደ በጐ ነገር ሲቈጠር ይስተዋላል። የሠርጉ ቀን “ኪዳን” እንደ ዋዛ
ተሰብሮ ወይም ኾን ተብሎ ተሰብሮ ወይም ከልክ ባለፈና በተደጋገመ ቸለተኝነት ተሰባብሮ፤ ሠርጉ ብቻ ደስታ፤ ትዳሩ ግን “የልቅሶ
አውድማ” የኾነባቸው ቊጥራቸው ቀላል አይደለም።
ከአገልግሎት በፊት ርስ በርስ መዋደድ ይቀድማል። ኢየሱስን ከመስበክ በፊት ሕይወቱንና ትምህርቱን በሚገባ
ማሰላሰል ብርቱ ማስተዋል ነው። ኢየሱስን እየሰበኩ ትህትናቸው የታይታ፣ ክርስቶስን በድንቅ ንግግር እየናኙ ኅብረት የሚጠየፉ፣ መዝሙረኛው፣
“አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።”
(መዝ. 55፥21) እንደሚለው፣ ልባቸውና አፋቸው የተጣላባት ግብዝ አገልጋዮችና አማኞችን እንደ ማየት ቅስም እንክት የሚያደርግ
ነገር ያለ አይመስለኝም።
መሲሐዊው የክርስቶስ መንግሥት ወንጌል ሰውና እግዚአብሔርን ብቻ ሳይኾን ሰውና ሰውን ወይም ጎረቤቱንም የማስታረቅ ዓላማ አለው። ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅቶ በመጥራት (ራእ. 5፥10) በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ በሰላም እንዲኖሩ ማስቻል የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ቀዳሚ ዓላማ ነው።
ለመንፈሳዊ ኅብረት በምሳሌነት እንዲያገለግሉ ከተጠቀሱት ምሳሌዎች መካከል፣ የሰውነት ክፍሎችን ወይም ብልቶች ናቸው።
እነርሱም የተለያየ ችሎታና ተግባር ተሰጥቶአቸዋል። ልክ እንዲኹ፣ በክርስቶስ አንድ አካል የኾኑ አማኞች፣ የተለያዩ ጸጋ፣ ስጦታና
ተግባር ተሰጥቶአቸዋል፤ “ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።”
(ሮሜ 12፥5) እንዲል።
እግዚአብሔር፣ ኀጢአትን እንደሚጠየፍ በግልጥ ከተናገረባቸው
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል አንዱ ክፍል ይህ ነው። ጠቢቡ የገለጣቸው ስድስት ኀጢአቶች በፍጻሜያቸው፣ መለያየትና ግጭት ብሎም
ወንድሞች እንዳይቀባበሉ የሚያደርግ ኀጢአት እንደ ኾነ መረዳት እንችላለን። በወንድሞች መካከል ጠብን ለማነሣሣት ወይም ለመዝራት
አስቀድሞ ሐሰተኛ ምላስ ትዋሻለች፤ መዋሸቷ ብቻ ሳይኾን ጠብን ለመጫር ሌሎችንም ማታለሏ አደገኛ ያደርታል።
ይህን ከላይ በርዕስነት የጠቀስኹትን ቃል የተናገረው
ስሙር አላምረው ይባላል፤ ባልሳሳት “ሊቀ ሊቃውንት” የሚል ማዕረግ ያለው ይመስለኛል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንግል
ማርያም ዙሪያ የሚሰጡት “ትምህርትና ስብከት” ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እያፈነገጠና መስመር እየሳተ ከመኾኑም ባለፈ፣ ድንግል ማርያምን
ታክከው የክርስቶስን መካከለኝነት በትክክል መንቀፍ ደግሞ የአደባባይ እውነት ኾኖአል፡፡
“ይሁዳ
ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ።” (ዮሐ. 13፥30)
ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል በአንዱ፣ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ “እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ” (ዮሐ. 13፥18-21) በማለት ከትንቢት ጠቅሶ ተናግሮአል። ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ወደ ደረቱ ተጠግቶ ለጠየቀው ሐዋርያ፣ “እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው ብሎ” መልሶአል፤ (ቊ. 26)። ይሁዳ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ፣ ጌታችን ኢየሱስ ነገረ ሥራውን ኹሉ እንዳወቀ ባረጋገጠለት ጊዜ፣ “… ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፦ ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ?” (ማቴ. 26፥14-15) ባለበት ቅጽበት፣ በሰይጣን ቊጥጥር ሥር ዋለ፤ “ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት” (ዮሐ. 13፥27) እንዲል።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ከቀረቡ ተወዳጅ መዝሙራት መካከል፣ የማርያም መዝሙር አንዱ ነው፤ የቅድስት ማርያም ዝማሬ የሚጀምረው እግዚአብሔርን በማመስገን
ነው (ሉቃስ 1፥46)። እግዚአብሔርን ስታመሰግንም፣ የአዳኝነት ሚናውን በግልፅና በትህትና በማሳየት ነው (ሉቃስ 1፥47)። መዝሙሮቿም
ከቅዱሳት መጻሕፍት ማለትም ከብሉይ ኪዳን ምንባባት የተቀዱና የተወሰዱ ናቸው።
“እነዚህ ነገሮች የሌሉት
ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።” (2ጴጥ. 1፥9 - 1954)
“እነዚህ ባሕርያት የሌሉት ግን የሩቁን የማያይ ወይም ዕውር ነው፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ
መንጻቱንም ረስቷል።” (ዐመት)
መጽሐፍ ቅዱስ “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት
አሁን ኵነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8፥1)፣ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤” (2ቆሮ. 5፥17) ብሎ መናገሩ
የታመነና የተረጋገጠ ሕያው እውነት ነው። ስለ መዳናችን በኀላፊ ንግግር ስንናገር እኒህ ኹለቱን መናገር እንችላለን፣ (1)
ድነናል (ኤፌ. 2፥8፤ ቲቶ 3፥6-7፤ ሮሜ 3፥24፤ 8፥24፤ 9፥30)፣ (2) ተቀድሰናል (ሮሜ 6፥24-25፤ 1ቆሮ.
1፥12፤ 6፥11፤ ዕብ. 10፥10፡ 14፤ 1ጴጥ. 2፥24)።
የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ የአይሁድን ሃይማኖት ሲከተሉ ኖረው፣ ፊታቸውን
ወደ ክርስትና ዘወር ስላደረጉ ሰዎች መልእክትን ሲጽፍላቸው፣ በቀደመው እምነታቸው ታላላቅና የሚከበሩ ነገሮችን ከኢየሱስ ጋር በማነጻጸር
“ኢየሱስ ከኹሉም[ከመላእክት፣ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ፣ ከመገለጦች ኹሉ፣ ከእንሰሳት መሥዋዕቶች] ይልቃል፤ ይበልጣል” በማለት በታላቅ
መገለጥ ይጽፍላቸዋል። ከዚህ ቀደም የተሠሩት ሥራዎች ኹሉ፣ በኀጢአት በወደቁት ነቢያት፤ አባቶችና እናቶች ፍጡራን አማካይነት መኾኑን
በመግለጥ በስፋት ይጽፋል። በርግጥም በብሉይ ኪዳን የነበሩት የእግዚአብሔር ሰዎችም፣ ስለ ሥራቸውና ጽድቃቸው ሲናገሩ፣ “ ..ሁላችን እንደ
ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ … ” (ኢሳ. 64፥6) ብለዋል።