ይሁዳ የክርክሩን መረጃ ከየት እንዳገኘ ባይነግረንም፣ በመንፈስ ቅዱስ
መነዳት እንደ ጻፈው ግን እናምናለን። ስለ ክርክሩ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ኹለት ጠንካራ ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ። እኒህም፦
1.
ዲያብሎስ እስራኤላውያንን ወደ ጣዖት አምልኮ ለመምራት የሙሴን አካል እንደ ጣዖት አምልኮ ሊጠቀምበት
ፈልጎ እንደ ነበር ይጠቅሳሉ። ሥጋውን አድርቀው እንደ ልዩ ኃይል እንዲጠቀሙበት ለማድረግ።
2.
ዲያብሎስ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ አካል ያለውን ዓላማ አስቀድሞ ገምቶ ሊኾን ይችላል፤ እና ዲያብሎስ ያንን
እቅድ ሊያከሽፍ ሞከረ። ሙሴ በኋለኛው ዘመን፣ በክብሩ ተራራ ከኤልያስ ጋር መገለጡን ብዙዎቻችን አንዘነጋም። ስለዚህ
እግዚአብሔር ለወደፊት እቅዱ የሙሴ አካል አስፈልጎታልና ዲያብሎስ እንዲወስደው አልፈቀደም።
ይሁዳ በመቀጠል ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር እንዴት እንደ ተከራከረ
ይነግረናል። ሚካኤል ተዋጊ መልአክ ነውና ዲያብሎስን "እግዚአብሔር ይገስጽህ" ብሎ በጽድቅ ተዋጋው እንጂ
አልተሳደበም። የዲያብሎስ አንደኛው ዕቅድ፣ የእስራኤል ልጆች የሙሴን ሥጋ ከአሕዛብ እንደ ተመለከቱት እንዲያመልኩት ማድረግ
ነበር። መልአኩ ግን ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ እንዲመለክ የማይፈቅድ ቀናተኛ ነውና ተቃወመው።
በርግጥ ሙሴ የታወቀ የፊተኛው ኪዳን መሪና ሊቀ ነቢያት ነው።
እግዚአብሔርን በተደጋጋሚ ቃል በቃል ያነጋገር የነበረ ነቢይ ነው። ግን ለኪዳኑ ሕዝብ እንደ ጣዖት እንዲኾን አልተፈቀደም።
ከሰሞኑ የሙሴና የማርያም ነገር ከክርስቶስ ቤዝወት ጋር ተያይዘው መከራከሪያ ኾነው ሲቀርቡ አይተናል። እስራኤል
ዓይናቸውን ከእግዚአብሔር አንስተው፣ የሙሴን ሥጋ ላይ እንዲያደርጉ ያኔ የጣረው ዲያብሎስ፣ ዛሬም
የክርስቶስን የመስቀል ቤዝወት፣ በማርያምና በሙሴ ለመከለል የፈለገ አይመስላችኹም?!
እግዚአብሔር ይገስጸው።
ewnet new እግዚአብሔር ይገስጸው።
ReplyDelete