Monday 4 January 2021

ውልደቱን ለ’ኔ ነው የምለው!

Please read in PDF

ጨለማ ነበርኩኝ የክፋት አበጋዝ

የሞት ልጅ አሽከሩ የአሳቹ ባለሟል

ኀጢአትና ዕድፈት የታሪክ አካሌ

ብልና ዝገትም የበላው መዝገቤ…

ለነበርኩት ልጁ

ለራቅኹት ከደጁ …

ዘመኔ ሲፈጸም ጨለማዬን ረግጦ

ሞትና ሲዖልን እንደ ሰም አቅልጦ

መጣ ተዛመደኝ ሰውነቴን ነሣ

በገዛኝ ጠላት ላይ በድል እያገሣ

ለዚህ ነው ውልደቱን ለ’ኔ ነው የምለው

በመንግሥቱ መምጣት ጮኼ ‘ምዘምረው!

3 comments:

  1. ተባርኬበታለሁ

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር አምላክ በነገር ሁሉ መከናወንን ይስጣችሁ። ብሩካን ናችሁ❤❤❤!!

    ReplyDelete