Monday 24 February 2020

ዘወረደ - መዋረድን ወድዶ …

Please read in PDF

ኪሩቤል ሱራፌል ክብራቸውን ጥለው
የሚዘምሩለት ለክብሩ ተነጥፈው

ሃያ አራት ካህናት ዘውድ አክሊላቸውን
ጌቶችና ኀይላት ንቀው ክብራቸውን
ʻሚንበረከኩለት ወድቀው ʻሚሰግዱለት …
ከሰማያት ወርዶ ገሊላ ተገኘ
ከመንበሩ ይልቅ መዋረዱ ናኘ።
መስቀሉን ጀመረ በማኅፀን አድሮ
ስለ ሰው ልጅ መዳን መዋረድን ወድዶ
የመሸነፍ አክሊል በፈቃዱ ለብሶ!
እንኪያስ …
በብዙ ውርደት ውስጥ አንሸማቀቅም
መንገዱ ነውና መስቀሉን አንስትም!

No comments:

Post a Comment