Thursday 13 February 2020

በነነዌ ማግስት!

Please read in PDF

በነነዌ ምድር …
ኀጢአት ተከተተ፣ ነውር ተከደነ
ዓመጻ ታለለ፣ ምሕረት ገነነ

የሦስት ቀን እንባ፣ ያʼምላክ ፊት መለሰ
የሰቀቀን እንባ፣ በሥርየት ታበሰ …
እኛ ግን …
ነነዌን ብንጾምም
ባንበላ ባንቀምስም …
አለን ተሞጅረን
በክፋት ታጅለን
በየዘመናቱ ነነዌን አስበን
ከነነዌ ይልቅ በዓመጻ ጸንተን…
እባክህ አዶናይ!
በያʼመቱ ጾመን ስላልተመለስን
ከመጾሙ በፊት ስጠን መመለስን!

No comments:

Post a Comment