Saturday 25 January 2020

“እኔነቴ”ን ልውደድ!

Please read in PDF

ራሴን አልወድም
አንተ ባየኸኝ ልክ “እኔ እኔን” አላይም
እናማ ጌታዬ!

እንደ ራስህ ውደድ አላወኩበትም፡፡
እኔ እኔን በመጥላት ታውሬአለሁና
እንደ ራሴ መውደድ አልቻልኩም በደህና፡፡
እባክህ አምላኬ …
ውዱን ባልንጀራ እንደ ራሴ እንድወድ
አንተ ባየኸኝ ልክ መጀመሪያ እኔ፣ “እኔነቴ”ን ልውደድ፡፡

1 comment: