Saturday 30 March 2019

ሙሽራው ሳይመጣ ...

Please read in PDF
የምጥ ጣ´ር አይሎ ክፋት ሲገነፍል
ኹሉም ወደ ጥፋት ፈጥኖ ሲንዶለዶል
የሌለ እስኪመስል የእውነት አሻራ

እምነት እየጠፋ ኀጢአት ሲበረታ
ጥጋ ጥጉ ኹሉ በነውር ተለውሶ
በዓመጻ ብዛት ዳሩ መሃል ኾኖ
ቢጎመዝዝ ጣዕሙ የመላ-ዓለሙ …
የሌለ እንዳይመስለን …
አለ በዙፋኑ አለ መድኅኑ፤
ዝም ያለ ቢመስል የመድኃኒት ክንዱ
ስላጠረ አይደለም የጌታ ማዳኑ …
ከጥፋት ልጅ በቀር ሁሉ ይድኑ ዘንድ
ጌታ ይዘገያል አይቸኩልም ለፍርድ!
ይልቅ ተመለሱ ፍጠኑ ቸኩሉ
ሙሽራው ሳይመጣ ሳይዘጋ በሩ!!!
                  

No comments:

Post a Comment