Wednesday 13 March 2019

ኹሉም ቀን ነው ቅድስት!

 አይሰልቸን ማዳኑ፣ ይተረክ ይሰበክ፤
የመስቀሉ ነገር፣ ኢየሱስ ይታወጅ፤
በቀናት በወራት፣ በዓመታት ሁሉ፤

ኢየሱስ አዋጅ ነው፣ አውጁ ለፍፉ፡፡
ሰኞና ማክሰኞ …፣ ቅዳሜና ሰንበት፤
ቀን እንዳትመርጡ፣ ወንጌሉን ለማወጅ …
ሕመምተኛ በዝቶ፣ በመላ ዐለሙ፤
ይናኝ፣ ይድረስ ወንጌል፣ በዲያብሎስ እስር ለታሰሩት ሁሉ፤
ወንጌሉን አብስሩ፣ ስበኩት በጩኸት፤

ኀጥእ ከተማረ፣ ኹሉም ቀን ነው ቅድስት፡፡

No comments:

Post a Comment