Sunday, 31 March 2019

ደብረ ዘይት - “መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” (ማቴ. 24፥3)

Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው መጥተው የነገረ ዳግም ምጽአቱን ምልክቶች ጠይቀውታል፡፡ ጌታ ኢየሱስና ደብረ ዘይት እጅግ “የተሳሰሩ” ናቸው፤ “እንደ ልማዱ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ” (ሉቃ. 22፥39) በተደጋጋሚ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ለጸሎትና በዚያውም ለማደር ይሄድ ነበር፤ (ዮሐ. 8፥1-2)፡፡ በዚያ አድሮ ማለዳ ማለዳ ከደብረ ዘይት ተነሥቶ አገልግሎትን ይጀምራል፡፡ “ድኃው” ኢየሱስ፣ ቤት ያልነበረው ኢየሱስ (ሉቃ. 9፥58) የጸሎት ስፍራውንና ማደሪያውን ያደረገው በደብረ ዘይት ነበር፡፡

Saturday, 30 March 2019

ሙሽራው ሳይመጣ ...

Please read in PDF
የምጥ ጣ´ር አይሎ ክፋት ሲገነፍል
ኹሉም ወደ ጥፋት ፈጥኖ ሲንዶለዶል
የሌለ እስኪመስል የእውነት አሻራ

Sunday, 24 March 2019

መጻጉዕ - ፈዋሹ እግዚአብሔር

Please read in PDF
“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” (ዘጸ. 15፥26)
   እስራኤል ከግብጽ ምድር ሲወጡ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በጸናች እጁ በተዘረጋች ክንዱ፤ በተአምራት አሻግሮአቸዋል፤ ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን ይዞ ለሦስት ቀናት የተጓዘው ወደ ሱርም ምድረ በዳ ነው፤ በዚያ ምድረ በዳ ላይ ሕዝቡ ውኃ ማግኘት አልቻሉም፤ ቀጥለው ወደ ማራ ቢመጡም የማራ ውኃ እጅግ መራራ ነበርና መጠጣት አልቻሉም፤ ከዚህ የተነሣ ታላቁን ተአምራት፣ ድንቁን ነገር በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ላይ የተመለከቱት እስራኤል፣ ባዳናቸውና በታደጋቸው አምላክ መታመንን ትተው፣ “ሕዝቡም፦ ምን እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ” (ዘጸ. 15፥24)። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ለመነ፣ ያህዌ ኤሎሂም እንዳዘዘውም አደረገ፤  ውኃውም ጣፈጠ።

Tuesday, 19 March 2019

ምኩራብ

  Please read in PDF
  አይሁድ ወደ ባቢሎን በምርኰ በወረዱ ጊዜ የቀደመው ኪዳን “የአምልኮ ማዕከል” ከኾነው ከመቅደሱ ተለያዩ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በሦስተኛው ዙር የምርኰ ማጋዝ በአካል ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ኢየሩሳሌም ገለበጣት፤ መቅደሷንም አፈረሰ፤ ከመቅደሱ ንዋየ ቅዱሳቱንም ዘረፈ፤ እስራኤልን ሙሉ ለሙሉ ባድማ አደረጋት።
   እናም የኪዳኑ ሕዝብ እስራኤል በምርኰ ሳሉ አምልኮ “ናፈቁ”፤ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ [በባቢሎን ጭምር] መቅደስ መሥራት ባይቻላቸው፣ በዚያው በምርኰ ባሉበት ምድር ኾነው የሚሰባበሰቡበትንና በዋናነትም ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡበትን፣ በንባብም የሚያመልኩበት ምኩራብ፣ በቁጥር አነስ ያሉ ሰዎችን ሊይዝ በሚችል መልኩ በሕዝቡ መካከል ሠሩ፤ እናም በምርኰ ምድር ኾነው በንባብ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ ሊታዘዙትም ምኩራብን ለሕዝቡ አቅራቢያ በኾነበት ስፍራ ተግተው ሠሩ።

Wednesday, 13 March 2019

ኹሉም ቀን ነው ቅድስት!

 አይሰልቸን ማዳኑ፣ ይተረክ ይሰበክ፤
የመስቀሉ ነገር፣ ኢየሱስ ይታወጅ፤
በቀናት በወራት፣ በዓመታት ሁሉ፤

Friday, 8 March 2019

ሰባት ዓመታት በጡመራ መድረክ (በብሎግ) አገልግሎት

   ኹሉም ነገሮቻችን በእኛ አቅም የተያዙ አይደሉም፣ መያዝም አይችሉም፤ በጌታ እግዚአብሔር ኹሉን ቻይነትና አለኝታነት ተደግፈው ያሉ እንጂ። የሕይወት እስትንፋሳችን እንኳ ተቀጥላ ያለችው፣ በእስትንፋስና በሕይወት ባለቤት በእግዚአብሔር መግቦት ብቻ ነው። ምሕረቱ ባይበዛልን፣ ቸርነቱ ባይገንልን፣ ፍቅሩ ባይትረፈረፍልን፣ ተግሳጹ ነፍሳችንን ባይመልሳት፣ ምክሩ ድካማችንን ባያበረታው፣ ማጽናናቱ ልባችንን ባይደግፈው … ገና ያኔ ገና በተዋጥን፣ የአዳኙ ወጥመድ ይዞን በጠፋን ነበር።

Tuesday, 5 March 2019

ከሰማይ በመውረዱ ራሱን ባዶ ያደረገ ኢየሱስ[ዘወረደ]

Please read in PDF
  ጌታ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ በመልበሱ፣ ከሰማየ ሰማያት ገሊላዊት ወደ ኾነችው የናዝሬት መንደር በመውረዱ፣ ከአንዲት በናዝሬት አገር ከምትኖር ድኃ ድንግል ሴት በመወለዱ፣ ኃጢአት በሚገዛው ዓለም በመመላለሱ … እጅግ ተዋርዷል። ይህን በማድረጉም በገዛ ፈቃዱ ራሱን ከራሱ ባዶ በማድረግ ለአባቱ ፈቃድ ፍጹም ታዟል።
 ጌታ ኢየሱስ ከሰማይ ወደ ምድር ወረደ ስንል፣ በአምላካዊ ማንነቱ ወይም በመንፈሱ ወዳልነበረበት ዓለም መጣ እያልን አይደለም፤ እርሱ ኹሉን የሚያውቅ (ዮሐ. 2፥24-25)፣ ኹሉን የፈጠረና የደገፈ ደግሞም፣ “ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል”፤ (ዮሐ. 1፥3፤ ቈላ. 1፥16፤ ዕብ. 1፥2-3) እንዲል፣ ኹሉ በኹሉ የኾነ፣ ጌታና የፍጥረት ኹሉ ባለቤት ነው። ምድርና መላዋ የእርሱና እርሱም ያለባት ናት፤ (መዝ. 24፥1)።

Sunday, 3 March 2019

“እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን?” (ኢሳ. 58፥3)

    እስራኤል በግልጥ ነውር ተይዛለች፤ በነውር የተያዘችው እስራኤል በሠራችው ኀጢአት ንስሐ መግባትና ራስዋን በጾም ክዳ ወደ አምላኳ ያህዌ ኤሎሂም መምጣት ሲገባት፣ እርሷ ግን ሃሰተኛ አምልኮ በማቅረብ፣ አምላኳን በሃሰተኛ አምልኮ ለመደለል፤ ለማታለል ፈለገች። በሰው አተያይ አምላክ የሚያይ መስሏት ኢየሩሳሌም ተታለለች፤ በታይታዊ የግብዝነት ሕይወት ትጾማለች ግን ጾሟ በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ አልነበረም፤ ሰውነቷን ታዋርዳለች ግን ውርደቷን በክብር የሚለውጥላት አንዳች የለም፤ ምክንያቱም ፈቃድዋን እንጂ የያህዌን ፈቃድ አትፈጽምምና።