Monday 4 December 2017

መልዐከ መዊዕ አባ የማነ ብርሐን ካሳሁን አፈርንሎት!

Please read in PDF

      በቀን 24/3/10 8:30 ገደማ በሻሸመኔ ከተማ ማኅበረ ኢየሱስ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ቀሚሳቸውን ለብሰው መስቀላቸውን ጨብጠው እንደጉባኤው እድምተኛ ከሌሎች ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ሰንበት ተማሪዎች ጋር በመኾን ልክ ጸሎት በሚጀመርበት ሰዓት ዱላና ድንጋይ አስጨብጠው ወደመድረኩ በመውጣት የያዙትን መስቀል ወደኪስዎ ከትተው ድብደባ ባርከው በማስጀመርዎ አፈርንሎት!

      እርስዎን የማውቅዎ 2004 . እኔ በወንጌል ጉዳይ ተከስሼ በእርስዎ ፊት ቀርቤ በብዙ ጩኸት ይከሱኝ ከነበሩት ከሳሾች በተሻለ ለዘብተኝነት ሲናገሩ ሰምቼዎ ነበር፤ የዚያኔ ጌታ ልብዎን "ለወንጌል አለዝቦ የሥጋ ልብ" እንዲያደርግልዎ በልቤ ማልጄዎት ነበር፤[ዲያቆን ለአባ ቆሞስ መጸለይ ያልተለመደ ቢኾንም¡] ዳሩ ግን ልብዎ ደንድኖ ጆሮዎ ከመስማትና ከማስተዋል ችላ ብሎ፣ በአመጸኝነትና በማን አለብኝነት የእርስዎን የግብር ልጆች አስከትለው በመምጣት፣ ወንጌል ሊማማሩ የተሰበሰቡትን የገዛ ልጆችዎን፣ "ተሳስተዋል ቢሉ መክረው አስተምረው መመለስ ወይም ባይቻልዎ ከእርስዎ ለሚሻል አባት ማስመከር ሲገባዎ" እጅና እግር ሰንዝረው ተማትተው ደም በማፍሰስዎ አፈርንልዎት!

      በዘመናት ወንጌልን ለማቆምና ለማጥፋት፣ ለማሳደድም ብዙዎች ቄሣሮች፣ አውግስጦሶች፣ አጼዎች፣ግለሰቦች፣ ጳጳሳት፣ ኮሚኒስት መሪዎች፣ ጦር ያነገቱ ባለሥልጣናት ... በተደጋጋሚ ተነስተዋል፡፡ ነገር ግን እንኳን ሊያስቆሙ ስፋቱን የሰደድ እሳት ያህል ያለከልካይ እንዲፈጥን አደረጉት እንጂ ሊያስቆሙት ፈጽሞ አልተቻላቸውም፡፡ ወንጌልን ሊያጠፉ የተነሡ ሁሉ ራሳቸው ስም አጠራራቸው እስኪጠፋ ተረሱ እንጂ ወንጌልን ሊያስቆሙት ፈጽሞውኑ አልተቻላቸውም፡፡

      የወንጌል ተቃዋሚዎች ለጊዜው በወንጌል የሚያምኑትን ሊያስሩ፣ ሊያሳድዱ፣ ሊደበድቡ፣ አካላቸውን ሊያጎድሉ፣ ሊፈነከቱ፣ ሊሳደቡ፣ ሊሳለቁ፣ ሊዝቱ፣ ሊዘብቱ፣ ጉባኤ ሊያስተጓጉሉ፣ የጸሎት ቤቶችን ሊያዘጉ፣ የዜማ መሣሪያዎችን ሊሠባብሩ፣ እንደጉድፍ ሊቆጥሯቸው ...እንደሚችሉ እናውቃለን፡፡ ምናልባትም "ሥጋቸውንም መግደል ይችሉ ይኾናል" (ማቴ.1028) ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይታሰርም፤ (2ቆሮ.29) እርስዎ ይህን ሃያል የእሳት ትንታግ በሥጋ አቅምዎ ሊይዙ በመነሣትዎ ስስ አቅምዎን አላወቁትምና አፈርንልዎት!

     ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ እንደኾንን፣ እግዚአብሔር እኛን አገልጋዮቹን  ሞት እንደተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኀለኞች እንዳደረገን፣ ስለክርስቶስ ሞኞች፣ አሳቾች፣ ያልታወቁ፣ ኀዘንተኞች፣ ድሆች፣ አንዳች የሌለን ብንሆን ስለስሙ እንናቅ ዘንድ ይገባናልና፤ (1ቆሮ.49 2ቆሮ.69 ሐዋ.541) በዚህ እጅግ ደስተኞች ነን፤ (ማቴ.511)፡፡ በሌላው ላይ እጁን የሚሰነዝር፣ ለመምታት የሚጋበዝ፣ የሚሳደብ፣ ሰውን የሚንቅ፣ የሚቆጣ ... እርሱ የተሸነፈና አቅመ ቢስነቱን በአደባባይ ያስመሰከረ ነው፡፡ እርስዎና አጋርዎችዎ እንዲህ ባለ ነውርና ሽንፈት በመያዝዎ አፈርንሎት!!!
      ለመኾኑ እንደእርስዎ የቱ ሐዋርያ ይኾን እጅ የሰነዘረው? የቱ ጻድቅ ነው እጁን ለቡጢ የጨበጠ? የቱ አባ ቆሞስ ይኾን የልጁን ደም ያፈሰሰ? የቱ ሰማዕት ይኾን ከመወገርና ከመደብደብ ይልቅ የወገረና የደበደበ? እርስዎ የማንን አሠረ ፍኖት ይኾን የተከተሉት? እንደኢየሱስና እስጢፋኖስ በሸላቶቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ዝምታን መምረጥ ከበደዎት ወይስ ጌታንና ሐዋርያትን በጥላቻና በንቀት እንዳሳደዱ አይሁድ "በታናናሾችዎ ላይ ተነሡ?!" ለመኾኑ ግን ምነው ወንጌል በጨበጡ ልጆችዎ ላይ ቀኝ ዓይንዎ ቀላ?!
      ወንጌል ኢየሱስ ነው፤ ወንጌልን ለማሰር መሞከር ኢየሱስን ጥፍንግ አድርጎ ለማሰር የመሞከር ያህል ነው፡፡ ስለዚህም በእርሱ የሚያምኑትን የሚያሳድዱና የሚጣሉ ጠባቸውና ጥላቸው ከራሱ ከኢየሱስ ጋር ነው፤ (ሐዋ.94)፡፡ ኢየሱስን የሚቃወሙ ሁሉ ደግሞ በስለት ላይ የመቆም ያህል ይጎዳሉ፤ (ሐዋ.95) በዐለቱ ኢየሱስ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፣ ድንጋዩ የሚወድቅበትም ይፈጨዋል፤ (ማቴ.2144) በፍጻሜው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ሁሉ ይደቅቃሉ፤ (1ሳሙ.210)፡፡ ይህን ሳያውቁ ቀሚስ ለብሰው መስቀል ጨብጠው "ወዲ ተጋዳላይ" በመሆንዎ አፈርንሎት!
እኛ ለእርስዎ ያፈርነው ክርስቲያን ነኝ ብለው በአይ ኤስ አይ ኤስ ተግባር በመገለጥዎ ነው! የሊቢያ አሸባሪዎችና በሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ ወገኖቻችንን ካረዱ አሸባሪዎች እርስዎ ግን በምን ይለዩ ይኾን?! እጅግ አፈርንሎት!
     እንዲህ ያለ ነገር ሳያውቁ በማድረግዎ ብናፍርሎትም፣ ጌታ ምሕረትና ይቅርታ ለእርስዎና ለባልንጀሮችዎ እንዲያደርግልዎ እንማልዳለን፡፡ በስሙ መከራ ያገኛችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ! ጸጋና ሠላም በጌታችን ኢየሱስ ይብዛላችሁ፤ አሜን፡፡


7 comments:

  1. Yih yihon zend gd new

    ReplyDelete
  2. በሌላው ላይ እጁን የሚሰነዝር፣ ለመምታት የሚጋበዝ፣ የሚሳደብ፣ ሰውን የሚንቅ፣ የሚቆጣ ... እርሱ የተሸነፈና አቅመ ቢስነቱን በአደባባይ ያስመሰከረ ነው፡፡ smart article

    ReplyDelete
  3. ውጊያው ከማን ጋር ነው??
    ክርስቶስ ለምን ተሰበከ ነው??? ከነሱ ጋር ያለው ክርስቶስ ከሁሉ በላይ ነዉ::
    ቁም ነገሩ: ከአልባሳቱ : አይመስለኝም: : ከእግዚአብሔር ጋር የሚጋፍ ሁሉ: ሲደቅቁ ትላንት አይተናል::

    ReplyDelete
  4. ያሳዝናል! ተዋህዶ ቤት እየሱስ ጌታ ነው ብሎ ማስተማር ከባድ ነው ተሃድሶ ትባላለህ ምን ትአለኝ የሃዋሪያት ስራ ላይ በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አላልናችሁም ብለው ጠየቋቸው በወህይኒ ሳሉ ከማለት ወደኃላ እንደማይሉ ነገሯቸው ጌታ አሁንም ጌትነቱን ይመሰከራል ዘመድኩን ማለት ባዶ ፣ቅናት የነገሰበት በገድልና በድርሳን የታጠረ " ወንጌል የተከደነበት" በአጋንት የተተበተበ ክፉ መንፈሱ ለሱ እውነተኛ ያደረገው ሰው ነው ተከታዩም አይፈረድበትም መፅሃፍ ቅዱስ አያነብም ሰው አንብቦለት የሚከራከር ተከታይ ያላት ተዋህዶ ለምን አይቅኑ ሰንበት ት/ት ቤት አይተነዋል ስለመላእክተ፣ፃድቃንሰማእታት ገድልና ከጌታ ውጭ የሆነ ዝማሬ የሚካሄድበት ነው ወንጌል የቀብር ቀን ይነገራል ከዛ ይከደናል።ላልተጠራንበት መትጋቱ፣ መስካሪዎቹን ማሳደዱ ወንጌል ለምን ተሰበከ ብሎ እንቅል ማጣቱ " ሰማዕትነት" መስሏችሁ ካሰባችሁ ጌታ ይቅር ይበላችሁ ።መስቀልም ሆነ ቀሚስ ቁስ ነው በልባችን የታተመው ጌታና ንጉስ የሆነው ነው ሻሼ ወጣት አዘንኩኝ ምክንያቱም ገብታችሁ ወንጌሉን ሰምታችሁ ከተሰጠነን ወንጌል ውጪ ከሆነ መጠየቅ እውነተኛው ዳኛ መፅሃፍ ቅዱስ ስለሆነ ያለዛ ምን የላከው ሞት አይፈራም ይባል የለም ማስተዋል አይጉደለን ማንም ይሁን በጌታ ምስክርነት የተጠራ ልናከብረው ይገባል ከወንጌል ውጪም ቢሆን ልናሳውቀው ነው ሚገባው ዘመድኩን ወንጌል ከተከደነበት እኛን ለመራን አይገባም እኛ እድለኞች ነን ጌታ ያስነሳቸው ለወንጌል ታጥቀው የተነሱትን ልንሰማ ተጠርተናል ።ወንጌል ያሸንፋል

    ReplyDelete
  5. ያሳዝናል! ተዋህዶ ቤት እየሱስ ጌታ ነው ብሎ ማስተማር ከባድ ነው ተሃድሶ ትባላለህ ምን ትአለኝ የሃዋሪያት ስራ ላይ በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አላልናችሁም ብለው ጠየቋቸው በወህይኒ ሳሉ ከማለት ወደኃላ እንደማይሉ ነገሯቸው ጌታ አሁንም ጌትነቱን ይመሰከራል ዘመድኩን ማለት ባዶ ፣ቅናት የነገሰበት በገድልና በድርሳን የታጠረ " ወንጌል የተከደነበት" በአጋንት የተተበተበ ክፉ መንፈሱ ለሱ እውነተኛ ያደረገው ሰው ነው ተከታዩም አይፈረድበትም መፅሃፍ ቅዱስ አያነብም ሰው አንብቦለት የሚከራከር ተከታይ ያላት ተዋህዶ ለምን አይቅኑ ሰንበት ት/ት ቤት አይተነዋል ስለመላእክተ፣ፃድቃንሰማእታት ገድልና ከጌታ ውጭ የሆነ ዝማሬ የሚካሄድበት ነው ወንጌል የቀብር ቀን ይነገራል ከዛ ይከደናል።ላልተጠራንበት መትጋቱ፣ መስካሪዎቹን ማሳደዱ ወንጌል ለምን ተሰበከ ብሎ እንቅል ማጣቱ " ሰማዕትነት" መስሏችሁ ካሰባችሁ ጌታ ይቅር ይበላችሁ ።መስቀልም ሆነ ቀሚስ ቁስ ነው በልባችን የታተመው ጌታና ንጉስ የሆነው ነው ሻሼ ወጣት አዘንኩኝ ምክንያቱም ገብታችሁ ወንጌሉን ሰምታችሁ ከተሰጠነን ወንጌል ውጪ ከሆነ መጠየቅ እውነተኛው ዳኛ መፅሃፍ ቅዱስ ስለሆነ ያለዛ ምን የላከው ሞት አይፈራም ይባል የለም ማስተዋል አይጉደለን ማንም ይሁን በጌታ ምስክርነት የተጠራ ልናከብረው ይገባል ከወንጌል ውጪም ቢሆን ልናሳውቀው ነው ሚገባው ዘመድኩን ወንጌል ከተከደነበት እኛን ለመራን አይገባም እኛ እድለኞች ነን ጌታ ያስነሳቸው ለወንጌል ታጥቀው የተነሱትን ልንሰማ ተጠርተናል ።ወንጌል ያሸንፋል

    ReplyDelete
  6. gena kemidritu lay tinekelalachu.kegzabher aydelachumna titefalachu

    ReplyDelete
  7. gena kemidritu lay tinekelalachu.kegzabher aydelachumna titefalachu

    ReplyDelete