Monday 11 December 2017

ባትናገር እንኳ …


ዕውቀትን የተራቀቁ
ሊቅነት የጠነቀቁ
ማስተዋል አለን የሚሉ

ጥበብን ያቀማጠሉ
ሐሳብን የተነተኑ
አንተን ግን ማየት ያልቻሉ…
                ዲዳ ይሁን፣ ትምክህታቸው
                ዝግ ይበል፣ ልቤ አያድምጣቸው
                የዚህ ዓለም ሞኝነት፣ ´የሱስ የ´ኔ አለኝታ
                ባትናገር  እንኳ፣ ሠላሜ ነው ለኔ፣ የፍቅርህ ዝምታ!!!


2 comments: