Thursday 18 August 2016

በዓይናችን አይተን!

Please read in PDF


ተረት መች ሆነና ብልሐታዊ ንግርት፣
የምሰብከውና የምንዘምርለት፣
አጉል ፍልስፍና ጥበብ መሰል ነገር፣

ከንቱ ልብወለድ ቃል አይደለም ክርክር፣
አይደለም ፤አይደለም የምንመሰክረው፣
በቅዱስ ፍርሃት ቆመን የምንጮኸው!
ከሰውና በሰው እንዳልመጣ አምነን፣
የምሥራች እያልን እንናገራለን፣
በቅዱስ ተራራው ከኢየሱስ ጋር ሆነን፣
የዘላለም እውነት በዓይናችን አይተን፡፡

No comments:

Post a Comment