Tuesday 24 February 2015

ቅዱስ ሰንበት



ሰንበት ማለት ዕረፍት
ዕረፍት ማለት ሰንበት
ከሆነ ትርጓሜው       

        እውነተኛ እረፍት
        የዘላለም ትፍስህት
         ከ'ርሱ በቀር ማነው?

እረኛ እንደሌለው
በጎች በመቅበዝበዝ
ያለን ተበትነን
      
          ወደ'ረፍቱ ጌታ
          ወደርሱ እንመለስ
          እንዲታዘንልን፡፡

ሰንበቴ ሆይ!
በየእሁዱ እኔ አልጠራህም
ታሻኛለህና ዛሬም ነገም፡፡

ዕረፍቴ ሆይ!
እንድገባ ወደርስትህ

ቅባት ነፍሴን በአዳኝ ደምህ፡፡ 

No comments:

Post a Comment