Wednesday 9 July 2014

ተበልጧል በሁሉ

Please Read in PDF

ትዳር ያቀለጠህ፣ ሥልጣን ያባለገህ፤
ሀብት ያሞላቀቀህ፣ ዝና ያሰከረህ፤
ዕውቀት ጨርቅ ያስጣለህ፤
ለዚህ አለም ነገር፣ የምትንቆራጠጥ፤
በሌላውስ ይቅር፣ በክርስቶስ ጌታ፣ በዚህ አትበለጥ፡፡

       ወዝህ የረገፈው፣ ቀለምህ ያለቀው፤
       ዓይንህ የባዘነው፣ አካልህ የሳሳው፤
       እጅህ የጨበጠው፣ ጣትህ የጠነቆለው፤
      ትናጋህ የጮኸው፣ ላንቃህ የተንቃቃው፤
       ለዚህ ዓለም ነገር፣ ከሆነ የዛልከው፤
       በነፍስህ ላይ ሥጋን፣ የዚያኔ ነው የሾምከው፡፡
እንኪያስ … !
ሥጋውን አትርፎ፣ ነፍሱን የሚያጎድል፤
ተበልጧል በሁሉ፣ የሞት ሞትን ሞቷል፤
በላይ በሰማይም፣ ህይወት ክብርን አ‘ቷል፡፡


1 comment: