"ማርያም ለኀጢአታችን ቤዛዊተ ዓለም አትባልም" ለሚለው ለአባ ገብርኤል ትምህርት ካራ ኦርቶዶክሳውያን እየሰጡ ያሉት ምላሽ፣ አስተማሪና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሳይኾን ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስና ከጳጳሱ ትምህርት በተቃራኒ የኾነ ምላሽ መስጠትን ተያይዘዋል። በምስሉ ከምትመለከቷቸው አንደኛው አባት "የርሷን ሥጋ ነውና የተዋሐደው የፈሰሰውም የርሷ ደም ነው" ይላል፤ ሌላኛው ደግሞ፣ "በመስቀል ላይ የዋለው ሥጋ የማርያም ሥጋ ነው" ይላል። በርግጥ በዚያ ቤት "ማርያም አራተኛ ሥላሴ ናት" የምንለው በምክንያት ነው።
በአንድ ወቅት አንድ ሰባኪ እንዲህ እያለ "ሰብኮ" ከመድረክ
ወረደና ከአንድ አባት ጎን ሄዶ ተቀመጠ። እኒያም አባት "ሰባኪውን" በቁንጥጫ መዠለጉት። ከዚያም "ሰባኪው"
ቁንጥጫው አመመውና ጮኾ፣ "ምነው?" አለ፤ እኒያም አባት "የቆነጠጥኹት ሥጋህ የእናትህ መስሎኝ ነው"
አሉት። የማርያምንና የኢየሱስን ሥጋ አንድ የማድረግ ትምህርት የ-ኑፋ-ቄ መዘዙ ብዙ ብቻ መኾኑ አይደለም። ጌታችን ኢየሱስ መከራ
መቀበሉንና መሰቀሉን ኹሉ ከንቱ የሚያደርግ ትምህርት ነው።
ኢየሱስ ከማርያም ሥጋ ነሣ ማለት፣ በኢየሱስ ኹለንተና የተከናወነው ኹሉ፣
በማርያም ኹለንተና ተከናውኖአል ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን በማንነቱ እንከን አልባና ወደር የለሽ፤ በሰማይም በምድርም
በሰውነቱ አንዳች ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ነው የሚያቀርበው። በግልጥም፣ ስለ ኢየሱስ ማንነት መጽሐፍ ቅዱስ ሲመሰክር፣
"ተንኰል የሌለበት" (ዮሐ. 1፥48)፣ "ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት" (ዕብ.
7፥26)፣ "ኀጢአት ያላወቀው" (1ቆሮ. 5፥21)፣ "ኃጢአት ያላደረገ፥ ተንኰልም በአፉ ያልተገኘበት"
(1ጴጥ. 2፥22)፣ "ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ" (ዕብ. 4፥15) ... ደግሞም ስለ ራሱ
ሲመሰክር፣ "ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?" (ዮሐ. 8፥46) "አንድ በደል ስንኳ ያልተገኘበት"
(ሉቃ. 23፥4፡14፡22) ብሎ ፍጹም መስክሮአል። ሥጋን ለብሶ በዚህ ልክ ከኢየሱስ በቀር በሰማይም ኾነ በምድር ምስክርነትን
የተቀበለ፤ ሊቀበል የተገባውም የለም፤ አይኖርምም።
በደልና ነውር፤ ነቀፋና ኀጢአት ያልተገኘበት መሲህ እንዳዳነን ስናምን፣
ከማርያም ሥጋን ከመንሣት ወጪ ከርስዋ የተቀበለውም፤ የሚቀበለውም አንዳች ነገር የለም። መጽሐፍ፣ "ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም
ቤዛነትም የተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ" (1ቆሮ. 1፥30-31) ነው ይላልና። እናም ክርስቶስ በፍጹም ሰውነቱ ተቤዥቶ
ነጻ አወጣን፤ መሥዋዕት ኾኖ ዕዳችንን ከፈለ፤ ንጹሕ ነውና ኀጢአትና ሞት ሊያገኘውም ሊይይዘውም አልቻለም ብለን እንመሰክራለን።
ምስክርነታችንም እውነት ነው!
ማርያምን ለሚያመልኩና ከክርስቶስ ጋር ለሚያስተካክሉ መንፈስ ቅዱስ ልባቸውን
ወደ ልጁ እንዲመልሱ በጽድቅ ይውቀሳቸው፤ አሜን።
መዝሙር 66
ReplyDelete¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
⁷ በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዓይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤ ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።
⁸ አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
⁹ ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ እግሮቼንም ለመናወጥ አልሰጠም።
እንደዚህ እውነቱን በአደባባይ በማፍረጥ ማርያምን አምላክ(የሴት አምላክ መሆንዋ ነው!!) ናት በማለት ውሳኔያቸውንና ማንን እንደሚያመልኩ ካሳወቁ ፤ ውሳኔያቸው ሊከበር ይገባል።የተስፋዬ ሞሲሳ እምነት ሁሉንም ኦርቶዶክሳዊ እንደማይወክል ግን ሊታወቅ ይገባል ።
ReplyDelete