በመጽሐፍ ቅዱስ
ከቀረቡ ተወዳጅ መዝሙራት መካከል፣ የማርያም መዝሙር አንዱ ነው፤ የቅድስት ማርያም ዝማሬ የሚጀምረው እግዚአብሔርን በማመስገን
ነው (ሉቃስ 1፥46)። እግዚአብሔርን ስታመሰግንም፣ የአዳኝነት ሚናውን በግልፅና በትህትና በማሳየት ነው (ሉቃስ 1፥47)። መዝሙሮቿም
ከቅዱሳት መጻሕፍት ማለትም ከብሉይ ኪዳን ምንባባት የተቀዱና የተወሰዱ ናቸው።
ማርያም ዝማሬዎቿን
የወሰደችው በአብዛኛው ከነቢየ እግዚአብሔር ልበ አምላክ ዳዊት ነው። ንጉሥ ዳዊት፣ ለደካሞች፣ ለተሰበሩ፣ ለተጐዱ ሰዎች ትኵረት
በመስጠት እግዚአብሔርን ያከብራል (መዝ. 136፥23፤ 138፥6)። ዓለም ለባለጠጎችና ባለ ሥልጣናት ትኵረት ብትሰጥም፣
እግዚአብሔር ግን ዓለም ችላ የምትላቸውን ሰዎች ይመለከታል። ከዚህ የተነሣ ቅድስት ማርያም፣
“የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤” (ሉቃ.
1፥48)
በማለት ትዘምራለች። አዎን
ማርያም፣ ገናና ዙፋን ከነበረው ከንጉሥ ዳዊት ወገን ብትኾንም ያ ቤተሰብ ግን ለብዙ ዓመታት ፈርሶ፣ በታላቅ መከራ ውስጥ እያለፈ
ነበር፤ ርስዋም ከዳዊት ንጉሣዊ ቤተሰብ የተገኘች ብትኾንም፣ ኑሮዋና መታጨትዋ አናጺ ከኾነ ሰው ዘንድ ነበር። ዳዊትን ከበጐች
በረት በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲኾን የመረጠው ያ ጌታ፣ ርስዋንም ከተዋረደችው መንደር ከናዝሬት ገሊላ መረጠ። ጌታ
እግዚአብሔር ዝቅ ያሉትን ከፍ ከፍ በማድረግ ደስ ይለዋል፤ ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር ይመርጣል፥ ኃያላኑንም
እንዲያሳፍር የዓለምን ደካማ ነገር ሁሉ የተናቀውንም ይመርጣል፤ ምክንያቱም ሥጋ የለበሰ ኹሉ በፊቱ እንዳይመካ፣ (1ቆሮ. 1፥27-29)።
ቅድስት ማርያም፣
የአምላክዋን መድኃኒትነት በመፈለግና በማግኘት ደስተኛ እንደ ኾነች ትናገራለች፤ ስለዚህም የተስፋው ፍጻሜ “ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ
እያለው እስራኤል ሊረዳ እንዳለ” በማስተዋልዋ ማለትም፣ እግዚአብሔር በመሲሑ በኩል ተስፋውን ኹሉ እንደሚፈጽም በማሰብ በአምላክዋ
ከመደሰት በቀር ሌላ የደስታ ምክንያት እንደማይኖራት አወቀች። ለዚህም ነው የመልአኩን ብሥራት በመቀበል፣ “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ
ይሁንልኝ” (ሉቃ. 1፥38) በማለት በፍጹም ትህትና የተቀበለችው።
ከዚህም የተነሣ፣
መልአኩ ገብርኤል (ሉቃ. 1፥30) እና ቅድስት ኤልሳቤጥ (ሉቃ. 1፥42) ማርያም መሲሑ በሥጋ ለመገለጡ “በተጫወተችው ሚና”
ከጌታ የተለየ በረከት እንዳገኘች ተናግረዋል። ድንግል ማርያም የእግዚአብሔርን ልጅ መውለድ ትልቅ ክብር እና ኃላፊነት እንደ ኾነም
ተረዳች። ይህ ትልቅ ሞገስም “ብፅዕት” እንደሚያስብላትም ተናገረች፤ አዎን በርግጥም ብፅዕት፤ ንዑድ የተመረጠች ናት፤ የጌታን ሥራ
ፈቅዳ በመቀበል ታዝዛለችና።
ከዚህ በተቃራኒ ግን ኦርቶዶክሳውያንና
ካቶሊካውያን ማርያምን በተመለከተ ያላቸው አቋም፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ሲታይ አያሌ ግር የሚያሰኝ ነገር አለው። ማርያም
ራስዋን ለእግዚአብሔር ሥራ በመገዛትና በመታዘዝ የገለጠችውን “የማገልገልና የባሪያነትን” ሕይወት የተለያየ ስያሜ በመስጠት፣
ከጌታ ጋር ሲያስተካክሏት አልያም ከፍጡራን ኹሉ የተለየች ፍጥረት ሲያደርጓት ይስተዋላል።
መጽሐፍም ራስዋ
ድንግል ማርያምም እንዳለችውም ግን፣ ርስዋ የጌታ ባሪያ ናት፤ ባሪያ መኾንዋ አንዳች የሚቀንስባት ነገር የለም፤ ይልቅ
ለእግዚአብሔር ፈቃድና ዐሳብ መታዘዝዋንና ለመፈጸምም እሺ ባይ መኾንዋን ያሳያልና። አስተውሉ፤ አንድም ሰው ክርስቶስ ኢየሱስ
እኛን ስለ ማዳን ባደረገው የማዳን ሥራ፣ “ባሪያና አገልጋይ” ተብሎ ሲጠራ አይከፋውም፤ መጽሐፍ ስለ መሲሑ ሲናገር፣ “የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ
ራሱን ባዶ አደረገ፥” (ፊል. 2፥7) ሲል፣ ማንም አይከፋውም፤ ምክንያቱም ራሱ ክርስቶስ፣ “የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን
ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።” (ማር. 10፥45) ብሎአልና። እንደ ባሪያ የታዘዘው ጌታ በሰማያት በግርማው
ቀኝ “በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በስሙ ይንበረከኩለት ዘንድ፥” ኹሉን አሸንፎ በሰማያት አለ፤ እናም የታዘዘው
ባሪያ በነቢዩ አንደበትም እንዲህ ተብሎለታል፤ “ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ … ጻድቅ ባሪያዬም
በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።” (ኢሳ. 41፥1፤ 53፥11)።
ያዳነን ጌታ በመታዘዙ ባሪያ ተብሎአል፤ ማርያም
“የጌታ ባሪያ” ብትባል በትክክል ለእግዚአብሔር ባሪያ ኾና እንጂ ሔዋንን ወክላ ወይም ሳትኾን ቀርታ አይደለም! እግዚአብሔር ምንም
እንኳ ያዳነንና የወደደን ቢኾንም ኹላችንም ወደን የተገዛንለት ባሪያዎቹና አገልጋዮቹ ነን! ይህን መኾን አንዳች ውርደት የለበትም!
“ጌታችንን ኢየሱስ
ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24) አሜን።
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እመቤታችን የተናገረችውን ዘወትር በውዳሴዋ ይደግሙታል። ይህም ፍቅርን ለመግለጽ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል እንዳለችው እናስባታለን። የአምላክ እናት መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ንጽህት ድንግል አማላጅ የመሳሰለውን እንላታለን። ይህንን ያደረገላት እግዚአብሔር እንደሆነ እናምናለን። አምላክ ናት ከአምላክ እኩል ናት ይላሉ የምትሉት እናንተ ናችሁ ።
ReplyDeleteእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከማህጸን ጀምሮ የጠበቃት እርሱ እራሱ እግዚአብሔር ነው ። የውርስ ሃጢያት ያላገኛት ናት
ReplyDeleteምነው ትውልድ ሁሉ ብጽት ይሉኛል የሚለውን አረሳኸው
ReplyDeleteብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንቶች እመቤታችንን እንደ አንድ ተራ ሰው አድርጋችሁ፣እንደ እናንተ አይነት ሰው አድርጋችሁ ታይዋታላችሁ።እርሷ ግን ከፍጥረት ሁሉ የከበረች ንዕድ ክብርት ናት፣ሰማይና ምድር አንድ ላይ የጸጉሯን ዘለላ አያህሉም።እውነት ነው እመቤታችን ለጌታ ባሪያው(አገልጋዩ)ናት እናቱም ናት፣ፈጣሪዋ ነው ልጇም ነው፣የእርሷ መጋቢ ሲሆን ከእርሷ ተመግቧል።
ReplyDeleteየጌታ እናት እንጂ ባሪያ አትባልም
ReplyDeleteAre bakh yetwld hulu estnfas nat....yegetam enat nechi
ReplyDeleteጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የፀነሰችው የወለደችው ያቀፈችው በድንግልና የተገኘ ጡቷን ያጠባችው በጀርባዋ ያዘለችው ከአገር አገር የተንከራተተችው እንደ ልጅ ያዘዘችው የላከችው እንደ እናት ያሳደገችው ያነጋገረችው እንደ ህጻን ሲወድቅ የደነገጠችው ..... እናቱ ናት። በዚህ ምድር ላይ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በድንግልና የወለደች ድንግል አምላኳን የወልደች እናት ከድንግል ጡት ያጠባች እናት አልታየችም ስለዚህ ትለያለች።
ReplyDeleteአምላኳን በየዕለቱ ጠዋት ስትነሳ እያየችው ማታ ስትተኛ እየተመለከተችው ያደረች እናት አልታየችም። ደህና አደርሽ ብሎ እናቱን አምላክ ሰላምታ ሲሰጣት አያስደንቅም እርሷም አምላኳን ጠዋት ስትነሳ ምን ብላው ይሆን? ደህና አደርክ? እርሱ የፍጥረት ሁሉ ጠባቂ ደህና አደርክ ትለው ይሆን ወይስ አምላኬ ፈጣሪዬ ጌታዬ ተመስገን ትለዋለች? ይህን ያደረገች የምታደርግም እናት የለችም። ታድያ ከፍጥረት ሁሉ አትለይም?
ሰማይ ዙፋኑ ምድሩ የእግሩ መረገጫ የሆነ እርሱ በማህፀኗ የታቀፈችው ድንግል ማርያም ብቻ ናት ምድርን በእጁ የያዘውን የታቀፈችው እርሷ ናት። እግዚአብሔርን ያየው አንድም እንኳ ማንም የለም እርሷ በየዕለቱ ታየዋለች ዓይን ሲገለጥ በመጀመሪያ ምታየው አምላኳን አምላካችንን ነበር። ይህ አይለይም? ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን የሚሸከሙትን እርሷ በጀርባዋ አዘለችው እነርሱ ማየት የማይችሉትን አምላክ ስታየው ኖረች። በደብረ ታቦር ክብሩን ሲያሳያቸው ያየነውን እርሷ በማህፀኗ ወሰነችው። ይህን ማን አደረገ ማንስ ሊያደርገው ይችል ነበር? ድንግል ማርያም ግን ወሰን ድንበር የሌለውን ሁሉን የሚወስነውን በማህፀኗ ወሰነችው። እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ቢያደርግ ሁሉን ቻይ ነውና ይቻለዋል። እመቤታችን ግን እንዴት ቻለችው?
መላኩ ያመሰገናት ኤልሳቤጥ ያወደሰቻት ነገሩ ቢደንቃችው ነው። አንዲት ድንግል ዓለምን ለማዳን ጌታ ከእርሷ እንዲወለድ የተገባች ሆና መገኘቷ ኖኅ በጥፋት ውሃ ዓለም ሲጠፋ የሰው ልጅ ዘር ከቶ እንዳይጠፋ ጻድቅ ሆኖ የተገኘው አንድ እርሱ ነበር።
ክርስቶስም ይወለድባት ዘንድ የተገባ ሆና የተገኘች በኢየሩሳሌም ከነበሩ ደናግላን ሁሉ በእግዚአብሔር የተመረጠች ቅድስት ድንግል ማርያም ነች። በእግዚአብሔር ከመመረጥ በላይ ምን ልዩ የሚያደርግ ነገር አለ። ለዚያውም እርሱን ፀንሶ ለመውለድ ለማጥባት ለማቀፍ ለማዘል ከእርሱ ጋር በየዕለቱ ለመዋልና ለማደር
እንደ ልጅ የታዘዛት እናት ማን አለች
ይህ ሁሉ ድንቅ ዕፁብ ከማሰኝት በላይ ምን አለ።
ሐዋርያቱን እንዴት እንዳከበራቸው እንመልከት እናቱን እንዴት ሊያከብራት እንደሚችል ማሰብ ቀላል ነውና
እርሷን እናቱን ከሌሎች ሰዎች ጋ ለማስተካከል የሚደረገው ጥረት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መላኩ አንቺ ከሴቶች መካካል የተባረክሽ ነሽ ብሎ ሲለያት እንመለከታለን ኤልሳቤጥም የጌታዬ እናት ወደኔ ትንሽ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ስር ድንቅ እናገኛለን።
መጽሐፍ ማርያምም ይህን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ይላል።
ታድያ እኔ ራሴን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ለማወዳደር ልቤ የሚነሳሳብኝ ትዕቢተኛው ማን ነኝ። ሃይማኖት በትህትና ራስን በማዋረድ ራስን ለእግዚአብሔር በመስጠት የሚኖርበት እንጂ ልታይ ልታይ ከሁሉ በልጣለው የሚባልበት ህይወት አይደለም።
ራሱን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋ ያወዳደረ ነገ ራሱን አምላክ ነኝ ብሎ እንደሚነሳ ምልክቱ ነው።
Be alem tarik laye tehadso tesakto ayakim lemin mesele ante mekawem bcha newu mtchelewu esti kerbeck mogtachewu zm blo mawurat aye menafkan tebanene bro
ReplyDelete