ጌታ እግዚአብሔር
በሉዓላዊ አምላክነቱ፣ ክፉውን ነገር ኹሉ ለክብሩ ሊጠቀምበት፣ ወደ በጎ እንደሚያመጣው እናምናለን፤ ኀጢአት እንኳ ከእግዚአብሔር
የሉዓላዊነት ወሰን አልፎ አያውቅም፤ እናም በምድራችን ላይ የምንሰማውን መለያየትና ጥቅመኝነትን ጌታ እግዚአብሔር አጥፍቶ፣
ለሕዝባችን መታነጽና ለክብሩ ታላቅነት እንዲሠራ ከኹሉ በፊት አስቀድመን እንማልዳለን።
አዎን! እግዚአብሔር የፈርዖንን ልበ ደንዳናነት፣ ለሕዝቡ ጥበቃና ትድግና እንደ ተጠቀመበት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው ስንል፣ በመላለሙ ላይ መጋቢና ሠራዒ፤ አስተዳዳሪና ጌታ ነው እያልን ነው፤ ስለዚህ የምድራችን ነገር የሚገደውና የሚያስብልን ተንከባካቢና ጻድቅ ጌታ አለን ማለታችንም ነው!