Monday 16 May 2022

ይድረስ ለየዋሁ ኦርቶዶክሳዊ ወገኔ በሙሉ!

 Please read in PDF

ያ ትሁት ልብ የነበረውና ጽድቅ ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ፣ 'የምታነበው ይገባሃልን?' ተብሎ በወንጌላዊው ፊልጶስ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው መልስ እጅግ ልቤን ይነካኛል። 'የሚያስረዳኝ ሳይኖር እንዴት ይገባኛል?' እኛ ከዚህ እውነተኛና ትሁት ሰው ደም ምንድነው የወረስነው? ከራሳችን ሰዎች እንዳንማር ተረግመን ይኾንን? ''በታሪካችን ውስጥ አንዳንድ ፋና ወጊ ወገኖቻችን ሃገርን የሚጠቅም እውነት ይዘው ብቅ ሲሉ ማጥፋቱን ተክነንበታል። (ምሳሌ፦ እነ ደቂቀ እስጢፋኖስን)። ለዚህ ነው በሥልጣኔ በር ላይ ቀድመን ደርሰን በመገተራችን፣ ሌሎች ከኋላ እየመጡ ቀድመውን የገቡት'' በማለት ፕሮፌሰር መስፍን በሕግ አምላክ ደቂቀ እስጢፋኖስ በሚለው የፕ/ር ጌታቸው መጽሐፍ ላይ የተናገሩት። 

መቼም ለሚያስተውል ሰው፣ የእኛ ታሪክ የሌሎች (አገሮች/ሕዝቦች) ታሪክ እንጂ የራሳችን እንዳልኾነ መገንዘብ ይቻላል። ለምንድነው ይህ ዓይነቱ ነገር የተጠናወተን? በእውነት የራሳችን የኾነ ታሪክ ሳይኖረን ቀርቶ ነውን? ነው ወይስ የራሳችንን ታሪክ እንደሚገባ ባለማወቃችንና ባለማክበራችን ይኾን? 

ጾማችን የሌሎች ሕዝቦች ጾም፣ ታቦታችንና የመቅደሱ አምልኮአችን የአይሁዶች፣ ሥራ አላሠራ ያሉን ቍጥር ስፍር የሌላቸው በአላቶቻችን የግብጾች፣ የደመራ ሥርዓአታችን የንግሥተ እሌኒ ታሪክ፣ የተጫነብን የምንኩስና ሥርዓት ተሰዓቱ (ዘጠኙ) 'ቅዱሳን' በሚባሉ ነጮች የተጫነብን፣ ቅዱሳን ብለን ታቦት እያባዛን የምናመልካቸው ሰዎች ጊዮርጊስ እንግሊዛዊ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ግብጻዊ (አቦ)፣ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ግብጻዊ)፣ አቡነ አረጋዊና ሌሎች ስምንት ጓደኞቻቸው ከኤሺያ የመጡ ወዘተ ናቸው።

ይህን ሁሉ ጉድ የተሸከመን ሕዝቦች ነን እንግዲህ፣ የራሳችን ታሪክ እንደሌለን የኾነውና በእነዚህ ባእዳን ታሪኮች ፋንታ ወደሚያኮራን የራሳችን የቀደመ ታሪካችን እንመለስ (እንታደስ) ሲባል አንዳንዶች በከንቱ ቍጣ የሚቆጡት።

እረ እባካችሁ፣ የሚያኮራ የወንጌል ክርስትና ጅማሬ የነበረን ሕዝቦች ነንና፣ የቤተክርስቲያናችንን የቀደመ ታሪክ አውቀን በሕይወት እንኑረው? ይህን የሚሉትን ወገኖች ማሳደዱ ምን ይጠቅማል? ለውጡ እንደ ኾነ የማይቀር መኾኑ ተረጋግጦአልና፣ የወንጌል ጠላት የኾነውን ክፉውን መንፈስ ማገልገላችሁ ያብቃ!! እናንተም ቆም ብላችሁ ለራሳችሁ ነፍስ አስቡላት። ጠባችሁ ከሥጋ ለባሽ ጋር ሳይኾን፣ የሚባላ እሳት ከኾነው አምላካችን ጭምር ጋር እንደ ኾነ አስተውሉ። ደግሞም የክርስቶስን ተከታዮች፣ አሳዳጅ ከነበረው የደማስቆው መንገደኛ ተማሩ፤ ለጥቅማችን ተጽፎልናልና በርቱ፤ ኹለንተናዊ ታሪካችንን አበላሽቶ እራሳችንን እንዳንኾን የተጫኑብንን ቡቱቶዎች ኹሉ በጋራ በመኾን ሙልጭ አድርገን እናስወግድና በራሳችን ታሪክና ማንነት ላይ አብረን ሰማያዊ መዝሙራችንን በከበሮና በጸናጽል እንዘምር?

ምነው፣ ክርስትና ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ነው ያደገው በሚል ስሜት፣ ሌሎችን 'መጤ' በማለት ስንሳደብ የኖርን ሰዎች ይህን ኹሉ መጤ ነገር የተሸከምን መኾናችንን እንዴት ማስተዋል አቃተን? ለነገሩ እውነተኛው ክርስትና በመጀመሪያ ከሰማይ ወደ እስራኤል (ዮሐ. 1፥12) ከዚያም ወደ ሌሎች አገሮችና ኢትዮጵያ የመጣ እንደ ኾነ ያስተውሏል (ማቴ. 28፥19-20)። ጌታ የጃንደረባውን ልበ ሰፊነት ለሕዝባችን ያድል፤ አሜን።

ጌታ ወደ ትክክለኛ ልባችን ይመልሰን። አሜን።

ሰላም ኹኑልኝ!

በጽዮን አገራችን ላያችሁ የምናፍቀው!

1 comment:

  1. BROTHERS, IF DO YOU WANT KNOW REGARDING THE BIBLE,
    1. PRAY TO HOLY GOD
    2. ASK LORD GOD TO KNOW ABOUT HIS WORD TO UNDER STAND.
    3. HOLY SPIRIT WILL SHOW YOU EVERY THING.
    HERE IS THE HOLY TRINITY ON THE BIBLE WRITTEN.
    Mathew 28;17 Therefore go and make disciples of all nations, baptizing them in the name of the Father and the Son and the Holy Spirit.

    to the writer Tesfa: you are simply a hopeless person. you have been writing many articles criticising our holy church. and to destroy it. but you can't. This great church is based on the blood of GOD, son of the virgin Mary. look how your sister protestant 'churches' are decaying and dying in the west where I am living because their teaching is false and satanic. you are repeating the same false teaching false prophecy. do you know what the end result of all your writing is? it is hell for eternity. becuase your Jesus is not the son of Theotokos but the false mesiah. do u understand ??? you are simply stupid protestant.

    ReplyDelete