Monday 8 February 2021

የችንካርህ ፍሬ!

 Please read in PDF

ድንግዝግዙ ኑሮ የጥልቁ ጨለማ

ክፋትን ናፋቂ ዓመጻ የተጠማ

ግብዝነት ልምዱ

ማስመሰል መንገዱ

ለኹለንተናዬ፣ ለከፋው መርቅዞ

ታየልኝ ችንካርህ ፍጹም ቤዛ ኾኖ!

ከዚህ የተነሣ …

ሞቴ ጎፈነነ፣ ገሃነም መረረ

ኀጠአትም በረሰ ሰይጣን ተባረረ

ሲኦል ድል መንሣቱ ኀይሉ ተወገደ

የዲያብሎስ ዙፋን መቀመቅ ወረደ

ስመጣ ወዳንተ ወደ ሕይወት አገሬ

ተወዳጁ ልጅህ የችንካርህ ፍሬ!

 

1 comment: