Monday 19 August 2019

ከኢየሱስ በቀር!

Please read in PDF
ሙሴ ቢናገርም ኤልያስ ቢያወራም፣
ጴጥሮስ ሦስት ዳስን ለመሥራት ቢነቃም፣
ከክብሩ ነጸብራቅ ከመንግሥቱ በቀር

አንዳች ሌላ ነገር በዚያ ስፍራ አልነበር!
ጴጥሮስ ዳሱን ጣለ፣ ኢየሱስን ያዘ
የአብ ድምጽን ሰምቶ ለኢየሱስ ታዘዘ፡፡
በኋለኛው ዘመን ሲነግረን አጽንቶ
በክብሩ ተራራ፣ ከኢየሱስ በቀር አላየሁም ከቶ!
ስለዚህ …
በሰው ልብ ታቁሮ የተወለደውን
አንሰማም ፍጹም የተፈጠረውን
በክብሩ ተራራ ሰምተን ያየነውን
እንመሰክራለን የአብ አንድ ልጁን!
              ጌታ ኢየሱስን፤ አሜን!!!

No comments:

Post a Comment