Thursday 15 February 2018

አንተ ባትወርድልኝ

ከመላእክት ዓለም ወደእንሰሳት በረት
ከመለኮት ሳታንስ ወደሰው ልጅነት

የባርያ መልክ ይዘህ የመጣኸው ጌታ
መውረድህ መዋረድ ቢኾንም ዝቅታ …
ለእኔ ሰውነት ግን ሙሌት ነው ከፍታ
ወዳʻንተ ለመፍለስ ወደክብርህ ቦታ፡፡
እንኳን ተዋረድከው ዝቅታን መረጥከው!
አንተ ባትወርድልኝ መች እኾን ነበር ሰው?!!!


1 comment:

  1. ....እንኳን ተዋረድከው ዝቅታን መረጥከው!
    አንተ ባትወርድልኝ መች እኾን ነበር ሰው?!!! wow nice article

    ReplyDelete