Saturday 6 January 2018

ታቹን አልርመጥመጥ!

መንቁር አፉን ነቅሎ
ጥፍሩን ኹሉ ጥሎ
ክንፉን እንኳ ሳይቀር ፍጹም አስወግዶ
በመለወጥ ሂደት መግል ቁስሉን ሽሮ
ዳግመኛ እስኪታይ በከፍታ በሮ

አንተ ነህ ሐድሶን የሰጠኸው ጌታ
የተሐድሶ መሪ የንስር አለኝታ!!!
ጌታ ሆይ!
ምሳሌው ለኔ ነው ለምወድኽ ልጅህ
በኃጢአት ቁስል ለተከበብኩልኽ
በገዛ ክፋቴ ክንፌን ላጣኹልኽ …፡፡
እባክህን!
ሥጋ የኀጢአት ጠባይ እንዳይንገሥ በላዬ
የውርደትን ኑሮ እንድጥል ከብልዬ
በኢየሱስ ልደት ዳግመኛ ውለደኝ
ታቹን አልርመጥመጥ በጽድቅህ ከፍ አርገኝ!!!
ሥጋ ሥጋ አልሽተት መንፈስህ ያውደኝ!!!
                                          አሜን፡፡


1 comment: