Wednesday 14 September 2016

... አዲስ ዘመን የለም



ቢግተለተል ዕድሜ፥ ምን ቢረዝም ዘመን፤
ተቆጥሮ ተሰልቶ፥ ቢሰጠን ብዙ ቀን፤

ካልከበረ ጌታ፥ ከ‘ኛ ጋር ካልኖረ፤
በቀን ሌሊታችን፥ ውሎ ካላደረ፤
የንጋቱን ኮከብ፥ ጸሐዩን ካላየን፤
አረጀነው እንጂ መች አዲስ ቀን አየን!!!

አዲስ ዘመን ጠባ፥ ሰው የሚባልለት፤
ወደአምላኩ ፊቱን፥ ዘወር ያ‘ረገ ’ለት፤
አልያ ግን ...
ዓመቱ ተባዝቶ፥ ብዙ ቢቆጠርም፤
ከክርስቶስ ወዲያ፥ አዲስ ዘመን የለም!!!

3 comments:

  1. እውነት እውነት

    ReplyDelete
  2. ከክርስቶስ ወዲያ፥ አዲስ ዘመን የለም
    በሚለው ሃረግ አልስማማም ምክንያቱም ክርስቶስ አምላካችን የመጣበት ዓላማ ስለ እርሱ ብቻ እንድናውቅ እንድንናገር እርሱን ብቻ እንድናምን ሳይሆን እርሱ እንዳለ እኔን ብታውቁ አባቴን ባወቃችሁ ነበር ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚወስድ የለም ከሚሉት የክርስቶስ ትምህርቶች ላይ ቤተክርስቲያናችን አልደረሰችም ያሰኛል። አባቶቻችን እግዚአብሔር እያሉ በማንኛውም ሁኔታ እና ግዜ የሚጠሩት ለዚህ ነው ባጭሩ።

    ReplyDelete
  3. ዓመቱ ተባዝቶ፥ ብዙ ቢቆጠርም፤
    ከክርስቶስ ወዲያ፥ አዲስ ዘመን የለም!!!

    ReplyDelete