Wednesday 7 October 2015

አንተ ስትደክም …


          Please read in PDF                     


ብትጠቁር ብትከሳ
ብትሞግግ በአበሳ
አጀቡ የሐዘን
ምትክህ ሰቀቀን …

መታገልህ መና
መሮጥህ ዕረፍት አልባ
ለእፎይታ ታግሰህ
ቢደራረብ መርዶህ
አበቃ ስትል እንደገና
ኃይሉን እያደሰ ቢመጣ መከራ
ቢቆለል ቢያስፈራ
ውል ጫፉም ቢጠፋ

ድንግዝግዙ ዳፍንት
ጭላንጭሉ ሙትት
ቀንህ የቁልቁሊት
ብትጓዝ ወደሞት
አክትሟል እንዳትል የ‘ኔ ቀን አብቅቷል
በርህን ስትዘጋ ጌታ ከደጅ ቆሟል
አንተ ስትደክም እርሱ ይጀምራል፡፡

No comments:

Post a Comment