ኢየሱስ የማናፍርበት ወንጌላችን ነው፤ ወንጌል ክርስቶስ ባይኖርበት “የምሥራች!” ተብሎ ሊሰበክ አይችልም፤ የቆምነው፤ ያለነው፤ የምንኖረው፤ የምንንቀሳቀሰው… እግዚአብሔር በክርስቶስ ካትረፈረፈው ጸጋ የተነሣ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ምንም ነን፤ ርሱ በምንም ነገራችን ውስጥ የገባ ምሉዕ አምላክና ሰው ነው፡፡
Friday, 29 November 2024
Thursday, 28 November 2024
ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? – (የመጨረሻ ክፍል)
መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣኑ
“ሲገሰስ”!
መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ዋና ማዕከልና የትምህርቶቹም ኾነ የልምምዶቹ መሠረት ነው። ይህ እንዲኾን ያደረገው ዋናው ምክንያት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሥልጣን ራሱ እግዚአብሔር ስለ ኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትኛውንም ትምህርት ወይም መጽሐፍ ይዳኛል፤ ይመዝናል እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከርሱ ውጭ በኾነ ትምህርትም ኾነ መጽሐፍ ፈጽሞ አይመዘንም፤ አይመረመርም።
Wednesday, 27 November 2024
ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? - ክፍል አንድ
የምዩጣኑ ጥርስ ያገጠጠ
ውሸት!
መንደርደሪያ
ጃንደረባው የተባለ ሚድያ የሠራውን ቪድዮ፣ ተመልክቼአለኹ፤ አሰላስዬዋለኹም። ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ የምጽፍበትን
መንገድ ሲያመላክቱኝ፣ ከነገሩኝ ሰዎች ተጽዕኖዎች ነጻ ልወጣ እንዲገባኝ ከራሴ መክሬአለሁ። በተለይም ደግሞ አንዳንድ ነገሮች፣
በቀጥታ ከእኔ ጋር የሚያያዙ በመኾናቸው ይህን ጽፌአለሁ። እጅግ በጣም አስነዋሪ ውሸቶችን ደግሞ ለማጋለጥ ስል፣ በግል የተደረጉ
የውይይት ቅጂዎችን ለመጠቀም ተገድጄአለኹ።
Tuesday, 12 November 2024
ጳጳሳቱና መታደስ የሚያስፈራቸው “ኦርቶዶክሳውያን”!
ከኦርቶዶክሳውያን
ጥቂት ጳጳሳትና መምህራን መካከል፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጠንከር ያሉ የተሐድሶ ድምጾች በተለያየ መንገድ እየተሰሙ ነው። በባለፉት
ወራት ፓትርያርክ አባ ማትያስ እንደ ተናገሩት፣
“ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።”
በማለት የሙስናና
የገንዘብ መውደድ ነገር ሥር የሰደደ መኾኑን ጠቁመዋል። በመቀጠልም ጳጳስ አብርሃም እንዲህ አሉ፣
“ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ኾናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም … ይህን አስነዋሪ ድርጊት እያወገዝን እውነትን ተላብሰን ከሙሰኞች የጸዳችና የከበረች
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል።”
በማለት ጠንከር ያለ
ድምጽ አሰምተዋል።
Friday, 8 November 2024
“መናፍቅ በመባሌ እጅግ ደስ ይለኛል”
“… በሥጋ ካየነው ያናድዳል፤ የሞተልንን
አምላክ በመከተል፣ ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔም ምሰሉ” ባለው መንገድ ከሄድን ያስደስታል፡፡
ምክንያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ … በአባቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተዋርዶአል፡፡ … ርሱ ምን የልተባለው ነገር አለ?
ዋናው ክሱ እኮ በሃይማኖት ነው፤ በሃይማኖት መከሰስ ማለት መናፍቅ ነው ተብሎ ነው፡፡ … ሰንበትን ሻረ፣ የእግዚአብሔር ልጅ
ነኝ አለ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ ብለው ነው፤ ያ ለነርሱ መናፍቅነት ነበረ … ርሱ ያልተባለው ምን አለ? …
ቅዱስ ጳውሎስ ምን ያልተባለው አለ? አስቀድሞ የብሉይ ኪዳን ዋና ጠበቃ ነበረ … ኋላ መንፈስ ቅዱስ አገኘውና ቀየረው፣ ጌታም
ምርጥ ዕቃዬ አለው፡፡ እነዚያ ግን መናፍቅ ነው ያሉት … በተለይ በነገረ ድኅነት እንዲህ መባሌ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡”
(ብጹዕ አቡነ በርናባስ ከመለሱት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)
Tuesday, 5 November 2024
የእግዚአብሔር መሰደብ ይሰማህ ይኾን?
የእውነተኛ ዓቃብያነ እምነት ሕመም!
በራሳችን ድካምና የኀጢአት ውድቀት የሚደርስብንን መናቅና ስድብ መታገሥ አንድ ነገር ነው፤ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔርና ስለ ስሙ መታገሥና መከራ መቀበል እጅግ ሌላ ነገር ነው። ዓለሙ በክፉ እንደ ተያዘ ለሚያውቅ አማኝ (1ዮሐ. 5፥19)፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመወገኑ ብቻ ለዓለሙና ለወገኖቹ መሳለቂያ ሊኾን ይችላል።ዘማሪው እውነተኛ ጻድቅ ነውና፣ ለሕዝቡ ኀጢአት ለማልቀስ ማቅ በለበሰ ጊዜ፣ እየተዘባበቱ ስቀውበታል (69፥11)፤ “በአደባባይ የሚቀመጡት ያሙኛል፤ ሰካራሞች በዘፈን ይሰድቡኛል” (ቊ. 12) እንዲል።