Monday 22 April 2019

እጅግ ረክሷልና!!!

Please read in PDF
ዓመት ሙሉ ታስሮ ባመቱ መፈታት
ወራት ሙሉ ወድቆ አንድ ቀን መነሳት
ለጊዜው መቆጠብ ለወራት መፈንጨት
በፋሲካ ሰሞን አማኝ አማኝ መሽተት

ፋሲካ አሳልፎ ከኀጢአት ጭን መሸጎጥ
ካንገት በላይ ታቦት ከዚያ በታች ጣዖት
እንዲህ ያለውን ኑሮ ክርስትና ብለን
ቁልቁል ተምዘግዝገን …
ቁልቁል የወረድነው
የኢየሱስን ትምህርት ወዲያ አሽቀንጥረን ነው
አቤቱ አሁን አድን አቤቱ አሁን አቅና
ክርስቲያን ነን ባዮች ተሳልቀዋልና!
ጅራፍህን አንሣ ግረፍና አጥራ
የጸሎቱ መቅደስ በግብዝነት መልክ
                          እጅግ ረክሷልና!!!

No comments:

Post a Comment