Monday 21 August 2017

ኾኜ ያንተ ሎሌ!

በዚህ በኛ ዘመን፣ ሁሉ ነቢይ ኾኖ፤
ሐዋርያነትም፣ ስሙ ብቻ ገኖ፤
ቅስናም ድቁናም፣ ሁሉ እየተካነው፤

ስሙን ተሸክሞ፣ ተግባሩን ኮነነው፡፡
እንዲህ ያለህ ነቢይ እንዲህ ያለህ መምህር
አልሻም መኾንን ጥንቅር ብሎ ይቅር …
እባክህ ጌታዬ፣
አንድ ነገር ስጠኝ፣ እርሱንም እሻለሁ፤
ላንተ መሰጠትን፣ ዘውትር ናፍቃለሁ፤
ልቅና ለፈቃድህ፣ ልፋታ ከቃሌ፤

ልስማህ ልታዘዝህ፣ ኾኜ ያንተ ሎሌ!

No comments:

Post a Comment