Friday 14 July 2017

ላ'ንተ ብቻ

የበገናው የመሰንቆው ኅብረ ዜማ
የዋሽንቱም የክራሩም የከበሮው ጥዑም ቃና
የግዕዛን ፉጨት የሕያዋን ቅኝት
የአምልኮ እልልታ የእንሰሳት የአራዊት
ላንተ ብቻ ይሁን ለክብር መንግሥትህ
ክብር ተጠቅልሎ አንተን ብቻ ያክብርህ!!!

የጉልበት መንቀጥቀጥ
የልቡና ፍርሐት
የነፍስ መራቆት
የመንፈስ መረታት
ስግደትና ቅኔ
ምስጋናና ምጽዋት
ላንተ ብቻ ይሁን
በፍጥረት ተወደህ ለምትኖረው ጌታ
ስላደረክልን ስለግሩም ሥራ ስለድንቅ ዉለታህ!!!
ፍጥረት አይሁንለት ምስጋና ዝማሬ የመንፈስ ፍርሐት

ላንተ ብቻ ጌታ ላንተ ቅዱስ ንጉሥ አምላክ ዘላለማት፡፡ 

No comments:

Post a Comment