Friday 22 July 2016

ትልቅ ነው አምላኬ

Please read in PDF

ከፍ ከፍ በል ጉላና ድመቅ
ወገብህን አጽና ዝናርህን ታጠቅ
መስባትንም ስባ
ለድልደህም ወፍር
ሙሉ ብረት ለብሰህ ሸልልና ፎክር
በል በልብህ ጀምር ከ’ኔ ማን ሊወደር?


እኔን እስትከልል በመጋረድ ስፋ
ውረስ የቻልከውን ከፈፋ እስከፈፋ
ጠላቴ ሆይ ቅና ጐልምስና ጠንክር
ልታጠፋኝ ፈርጥም ብዙ ተገዳደር
ግና
አናቴን ልታፈርስ ቀስት ስታነሳ
ፈጽሞ ፈጽሞ ፈጽሞ እንዳትረሳ

ካ‘ንተ በላይ ገኖ
ፍጹም መጥቆ ልቆ
በብረት በትሩ ከ‘ግሬ ሥር ‘ሚጥልህ

ትልቅ ነው አምላኬ የሚደለድልህ፡፡ 

No comments:

Post a Comment