Saturday 14 May 2016

ብርሃን ትሆኑ ዘንድ


ያ አሮጌው አዳም ፍጥረትን አስረጀ
በልዞ ቸክኮ  ፤ በኃጢአት ሸለቆ ዘመናትን ፈጀ
አልታዘዝንምና፦ እኛንም አገኘ ፤

ባልሠራነው በደል በደለኞች ሆነን
ተኰነን በአንድነት እንደ‘ርሱ ተቆጥረን፡፡

ሁለተኛው አዳም ዳግመኛ ሊያገኘን
ሥጋ ለብሶ መጣ እኛንም መሰለን ፤
ከኃጢአትም በቀር ሁሉንም አድርጐ
ሕይወት ጽድቅን ሰጠን በመንፈሱ ወልዶ፡፡

ከዚህ የተነሳ ነው ...
በ‘ርሱ ሥራ እኛ ጸድቀናል ፤ ድነናል ደፍረን የምንለው፡፡                           

በዚህ ብንመካም ደግሞም እንሮጣለን
የፊቱን ልንጨብጥ የኋላውን ትተን
ደምን እስከማፍሰስ እንጋደላለን
ዝም አንልም ከቶ የጽድቅን ትጥቅ ታጥቀን፡፡

እናንት ...
ኃጢአት የለብንም ብላችሁ ‘ምትኰሩ
ብርሃን ትሆኑ ዘንድ፥ ኖሮ ያሳየንን የ‘ርሱን ሥራ ሥሩ፡፡



No comments:

Post a Comment