Saturday 25 July 2020

ቀናነት እንዳንተው!

Please read in PDF


ደም እንዳሰከረን ደም እንደ ተጣባን
እንደ ንዳድ ወርሶ ቂም እንዳጐበጠን

የደም ጋኔን ይዞን ደርሶ እንዳደባየን
አብሮነት ጐፍንኖን መዋደድን ጠልተን
አለን በትእቢት ደም እንደ ጨበጥን…፡፡

እባክህ አዶናይ እባክህ አንድዬ
አስጥለን ከደም ሰው ከክፋት ጉባኤ
ምድራችን ጨቅይቷል በደም ተበክሏል
ዘመናችን በደም ተነክሮ አልሏል
እባክህ ነጻ አውጣን እባክህ አጥልለን
ከደም ጨላጮች ጋር በአንድ አትኰንነን
ቀናነት እንዳንተው በምክርህ ገስጸን፡፡


1 comment: