ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)
መግቢያ
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የኾነኝ “ቀሲስ” ዳንኤል ክብረት የተባለ ሰው፣
በebs tv በአርአያ ሰብ(Who is Who) ፕሮግራም ላይ፣ በቀን 19/9/2010 ማታ 2፡00 ሰዓት ገደማ ላይ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን
በተመለከተ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ፍጹም ሸፍጥና ክፋት የተሞላበትንና ከታሪክ እውነታ ያፈነገጠ ሃሳብን በማቅረቡ፣ እውነታውን ከቤተ
ክርስቲያኒቱ መጻሕፍትና ከአባቶቿ አንደበት ማሳወቅ አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱና ነው።
ስለዚህም ጽሑፉ ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪካዊ ዳራ ይልቅ እጅግ በአመዛኙ
በእነርሱ ላይ የተፈጸመውና ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍቶቿ የያዘቻቸው እውነት ከቅዱሳት መጻሕፍት[1][ከመጽሐፍ
ቅዱስ] አንጻር እንዴት ይዳኛል? ዳንኤል ክብረትስ ምን የተለየ ሃሳብን በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዙርያ ይዞ ብቅ አለ? ይዞ ብቅ
የማለቱ እሳቤስ ምን መዘዝ አለው? ቅዱሳት መጻሐፍትስ እንዴት ይዳኙታል? ዳንኤልና ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ያህል ጥብቅ ዝምድና አላቸው?
ዳንኤል በማናቸው ምክንያትስ ቢኾን የሰው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል የሚገደው ነውን? … የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ኹኔታዎችን በአጭሩ
ለመዳሰስ እንሞክራለን።