Thursday, 28 December 2017

የማይለወጠው ዥንጉርጉሩ ነብርና የኢትዮጲያዊ መልክ

 ነቢየ እግዚአብሔር ኤርምያስ፦ “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡” (ኤር.13፥23) በማለት፣ ስለይሁዳ ኃጢአት በከባድ ወቀሳ ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ይሁዳ ተጠራርጋ በእግዚአብሔር ፍርድ ልትጠፋ እንዳለች በእግዚአብሔር ስለተረዳ፣ ሚስትን ከማግባትና ልጆችንም ከመውለድ ተከልክሏል፤ (ኤር.16፥1-4)፡፡ ትዳር ብቻም ሳይኾን ወዳጆቹም እጅግ ጥቂቶች ነበሩ፤ አኪቃም (26፥24)፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስና (39፥14) ኢትዮጲያዊው አቤሜልክ ናቸው (38፥7)፤ የክፋቱ ጠጣርነት ከሰው በብዙ ስላገለለው ረጅም ዘመኑን ያሳለፈው በሐዘን ነው፡፡
     የይሁዳ ኃጢአቶች የተገለጡና ለኹሉ የታዩ ነበሩ፤ “ይሰርቃሉ፥ ይገድላሉ፥ ያመነዝራሉ፥ በሐሰትም ይምላሉ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ይገፋሉ፥ በቅዱሱም ስፍራ ንጹሕ ደምን ያፈስሳሉ፥ ስሙም በተጠራበት በቤተ መቅደሱ በፊቱ ቆመው፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም ብለው ይክዳሉ፣ ስሙ የተጠራበት ቤት በዓይናቸው ፊት የሌቦች ዋሻ አደረጉት፣ የቀደሙት አባቶቻቸው እግዚአብሔርን ተዉ፣ አመነዘሩ፣ አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው አማልክትን አድርገው፣ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም፥ ያስቈጡትም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል አጠኑ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን አፈሰሱ፣ ሕጉንም አልጠበቁም፤ እንዲኹም እነርሱም ከአባቶቻቸው ይልቅ ክፉ አድርገዋል፤ እነሆም፥ ሁላቸውም እንደ ክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄደዋል እርሱንም አልሰሙትም” (7፥1-11፤ 16፥11፤ 20፤ 22፥9፤ 23፥10፤ 32፥29፤ 44፥2፤ 23)፡፡ በዚህ ኃጢአታቸው እግዚአብሔርን ፈጽመው አስቆጥተውታል፡፡

Tuesday, 26 December 2017

በጋሻው “አፍንጫው ሲነካ[ስሙ ሲነሣ]፣ ዓይናችኹ ላላቀሰ” ኹሉ!



Please read in PDF
    በግልጽ አንድ ያልተግባባነው ነገር አለ፤ የሐሰት ትምህርትን መቃወምና የሐሰት መምህራንን አለመቀበል የወንጌል ልብ አለመያዝ ወይም በወንድም ላይ መፍረድ ማለት አይደለም፡፡ ለበጋሻው ሳልራራለት ቀርቼ አልነበረም የሐሰት ትምህርቱን የተቃወምኩት፡፡ “አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ፤” (ይሁ.22-23) የሚለውን የቅዱስ ይሁዳ ቃልም ፈጽሞ ጠፍቶኝ ወይም ተዘንግቶኝ አይደለም፡፡
  ብናስተውል፣ የሐሰት ትምህርትን እንደቃሉ መቃወም እውነተኛ አማንያን እንዲጠበቁና እንዲጠነቀቁ ማድረግ ብቻ ሳይኾን፣ ሐሰተኛውን መምህር እንዲመለስ ተግሳጻዊ በኾነ መንገድ “የመማጸንም ሥራ” ነው፡፡ ትምህርቱን ስንቃወም ሰውየውን[የሐሰት አስተማሪውን] ከመጥላት ጋር አይደለምና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ የነበረውን የታወቀውን አመንዝራ ሰው፣ “ … እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው” ሲል፣ ከጥላቻና መዳኑን ካለመፈለግ አንጻር ሳይኾን፣ “  መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ” ነው፤ (1ቆሮ.5፥5)፡፡

Monday, 11 December 2017

ባትናገር እንኳ …


ዕውቀትን የተራቀቁ
ሊቅነት የጠነቀቁ
ማስተዋል አለን የሚሉ

Thursday, 7 December 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፮


Please read in PDF
የእምነት ቃል አገልጋዮች የሰውን ሰው-ነት ለመካድ የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች
   መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሥጋም መኾኑን ቢናገርም፣ የቃል እምነት አገልጋዮች ግን ይህን እውነት ከዓውድ ውጪ አጥምመው “ሰው መንፈስ ነው ለማለት” የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች አሏቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹን ከዚህ በታች እያነሣን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ እንሰጥበታለን፡፡
·        ፍ.1፥26-27 እና 2፥7፦ እኒህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ ተመልክተናልና የቀደሙትን ክፍሎች እንድትመለከቱ በመጋበዝ አልፌዋለሁ፡፡ “ሰዎቹ” ሰውን “መንፈስ ነው” ለማለት ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች መካከል መኾናቸውን ግን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡
·        ሐ.3፥1-13፦ ሰውን አመናፋሾቹ የሐሰት መምህራን ከዘፍጥረት መጽሐፍ ቀጥለው የሚንደረደሩት ወደዚህ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ እንግዲህ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዓውዳቸው ለማያጠና ተማሪ፣ “እምነትና በጎ ሕሊናውን ያስጥሉታል፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር እንዲጠፋ ያደርጉታል፤” (1ጢሞ.1፥19)፡፡ ስለዚህ “ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ እንደማይችሉ ሞኞች ሴቶች፣ ከተነዳላቸው ወደየሞት ወጥመዳቸው ሰተት አድርገው ያስገቡታል፤ እኛ ግን ስለምንሰማው ነገር ልንጠነቀቅ፤ ባለማስተዋልም ልንዘለል አይገባንም፤ (2ጢሞ.3፥6-7)፡፡

Monday, 4 December 2017

መልዐከ መዊዕ አባ የማነ ብርሐን ካሳሁን አፈርንሎት!

Please read in PDF

      በቀን 24/3/10 8:30 ገደማ በሻሸመኔ ከተማ ማኅበረ ኢየሱስ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ቀሚሳቸውን ለብሰው መስቀላቸውን ጨብጠው እንደጉባኤው እድምተኛ ከሌሎች ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ሰንበት ተማሪዎች ጋር በመኾን ልክ ጸሎት በሚጀመርበት ሰዓት ዱላና ድንጋይ አስጨብጠው ወደመድረኩ በመውጣት የያዙትን መስቀል ወደኪስዎ ከትተው ድብደባ ባርከው በማስጀመርዎ አፈርንሎት!

      እርስዎን የማውቅዎ 2004 . እኔ በወንጌል ጉዳይ ተከስሼ በእርስዎ ፊት ቀርቤ በብዙ ጩኸት ይከሱኝ ከነበሩት ከሳሾች በተሻለ ለዘብተኝነት ሲናገሩ ሰምቼዎ ነበር፤ የዚያኔ ጌታ ልብዎን "ለወንጌል አለዝቦ የሥጋ ልብ" እንዲያደርግልዎ በልቤ ማልጄዎት ነበር፤[ዲያቆን ለአባ ቆሞስ መጸለይ ያልተለመደ ቢኾንም¡] ዳሩ ግን ልብዎ ደንድኖ ጆሮዎ ከመስማትና ከማስተዋል ችላ ብሎ፣ በአመጸኝነትና በማን አለብኝነት የእርስዎን የግብር ልጆች አስከትለው በመምጣት፣ ወንጌል ሊማማሩ የተሰበሰቡትን የገዛ ልጆችዎን፣ "ተሳስተዋል ቢሉ መክረው አስተምረው መመለስ ወይም ባይቻልዎ ከእርስዎ ለሚሻል አባት ማስመከር ሲገባዎ" እጅና እግር ሰንዝረው ተማትተው ደም በማፍሰስዎ አፈርንልዎት!

Saturday, 2 December 2017

የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፭

ü  ዘፍጥ.2፥7 
     ህ ክፍል የምዕ.1 ሌላ እይታ ወይም ማብራሪያ እንጂ ከስድስቱ ቀናት ውጪ ቀጣይ ታሪክን በራሱ የያዘ አይደለም፡፡ የፍጥረትን ታሪክ በተመለከተ ከሁለት አቅጣጫ በመመልከት ወይም የምዕ.1ን የአፈጣጠር ሁኔታ ለማብራራት የተቀመጡ እንጂ፣ ሁለት የተለያዩ ዘመናት ታሪኮችና ክስተቶች አይደሉም፡፡ ይህ ደግሞ የቅዱሳት መጻሕፍት ባሕርይ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ አንድ ሰው “ከመሬት ተነሥቶ” አራቱ ወንጌላት ይበዛሉና ይቀነሱ ቢል፣ ጤናማ ሃሳብ ነው ብለን አንቀበለውም፤ ምክንያቱም የአንዱን የጌታችን ኢየሱስን ትምህርትና ሕይወት ከአራት ወንጌላውያን እይታ አንጻር አይተው አስፍረውታልና በደስታ ተቀብለነዋል፡፡ በዘፍ.1 እና 2 ላይም አንድን የፍጥረት ታሪክ በሁለት እይታ መስፈሩን ማስተባበል አንችልም፡፡ 
    አልያ ግን አሁንም ሌላ ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን፤ “እግዚአብሔር ፍጥረትን በስድስት ቀን ፈጥሮ አልጨረሰም” ወደሚል አንድ እንግዳ ጫፍ ይወስደናል፡፡ ስለዚህ ምዕ.2 የምዕ.1 ማብራሪያ ወይም ሌላ እይታ ነው፡፡[1] ይህንንም እንዲህ በአጭሩ ማሳየት እንችላለን፤
ü  ለሰማይና ምድር፦
v ምዕ.1፥1-2 በአጭሩ፣ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡ ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር” ይላል፤
·        ምዕ.2፥4-6 ላይ ይኸንኑ ሲያብራራ፣ “እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው፡፡ የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር” ይላል፡፡