Saturday 16 March 2013

ሰንበት


Please read in PDF


ቀኑማ ቀን ነው አንዱ ሌላን ይከተላል
ተደጋግሞ ሣይጨመር ሳይቀነስ ይከሰታል
ሰኞ ያው ነው ከእሁድ የለው ልዩ
መለኪያ መብለጫውን አጥብቀው ካላስተዋሉ
እስራኤል ቀን ሲያመልኩ ሳይለዩ መባረኪያውን
ፈት ሆነው ከመልካም ሥራ ገነዙት ራሳቸውን
በጉድጓድ ግልገል ወድቆ
በወህኒ እስረኛው ማቆ
በደጁ ድሀ ተርቦ እጅጉን በጣም ተጠምቶ
ወገኑ የሚልሰው አጥቶ

በህመም ለሚያቃስተው
ሞት ከብዶት ላጎነበሰው
በነብሱ ለተራቆተ
ንጣቱ ለመነቸከ
ለገዛ የስጋ አብራኩ
ለብጤው ለእንደርሱ አይነቱ
ሰንበት ነው ልረፍ እያለ
ስንቱ ነው ስንት የገደለ
ሰንበቱ ቅዱስ እንዲሆን
እንድታይ ፍጹም እረፍትን
ሸክሙን የወንድምህን
አራግፈው ያደከመውን
ያን ጊዜ እረፍትህ ሆኗል
በጌታ ቀንህ ተባርኮ እንደወንዝ ሠላምህ ፈሷል፡፡

1 comment:

  1. Wendme! Satjemr minew akomk? Indatitegna bertiteht nika.

    ReplyDelete